1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የላምፔዱዛ ስደተኞች

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 26 2003

የኢጣሊያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ይፋ እንዳደረጉት፤ በአንዲት ወደ ሶስት መቶ የሚጠጉ ስደተኞችን ባሳፈረች የአሳ አጥማጆች ጀልባ የ25 ሰሜን አፍሪቃውያን አስክሬን አግኝተዋል።

https://p.dw.com/p/Rda3
የላምፔዱዛ ሟች ስደተኞችምስል picture-alliance/dpa

ሟቾቹም አየር በማጣት ታፍነው ህይወታቸው እንዳለፈች ነው የተገመተው። ስደተኞቹ እሁድ ማምሻውን ከላምቤዱዛ ደሴት 50 ኪሜ ርቀት ላይ የድረሱልን ጥሪ አሰምተው እንደነበር ተገልጾዋል። የሟቾቹ ስደተኞች ዜግነት እስካሁን አልተረጋገጠም።

ከ25ቱ አስክሬን መካከል አብዛኞቹ ወጣት ወንዶች ናቸው። በአንድ የጀልባይቱ የመሳሪያ ክፍል ውስጥ ነበር የተገኙት ፤ ምንም አይነት የኃይል እርምጃ እንዳልተወሰደባቸው ለማወቅ ተችሏል። የሚገመተው ሟቾቹ ከሶስት ቀናት በፊት በንፁህ አየር እጦት እና ከጀልባይቱ ሞተር በወጣው ጢስ ታፍነው ህይወታቸው እንዳለፈች ነው።

ዳኒኤላ እሽታል

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ