1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የልማት ርዳታ፤ የምዕራቡ ዓለምና የኤርትራ ግንኙነት

እሑድ፣ መጋቢት 20 2007

ራሷን የቻለች ሀገር ከሆነች ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረችዉ ኤርትራ ከምዕራቡ ዓለም መንግሥታት ጋ ያላት ግንኙነት የቀዘቀዘ መሆኑ የሚታይ ነዉ። ምሥራቅ አፍሪቃዊቱ ትንሽ ሀገር በአቅራቢያዋ ከሚገኙ ሃገራት ጋ ያላት ግንኙነትም የሞቀ የሚባል አይደለም።

https://p.dw.com/p/1Eyie
21.01.2013 Karte Eritrea Asmara eng

ይህን የመሳሰሉ ነገሮች ተደማምረዉም ኤርትራን የተነጠለች ሀገር ቢያስመስላትም፤ የወጣቶቿ በገፍ መሰደድ፤ የብዙ ጋዜጠኞቿ እና የፖለቲካ ተቃዋሚዎች መታሠርና ደብዛቸዉ መጥፋቱ ስሟን በየጊዜ የሚያስጠቅሱ ምክንያቶች መሆናቸዉ አልቀረም። እንዲህ ዓይነቱ አሉታዊ ጉዳይ ቢኖርም የሀገሪቱን መንግስት በልማት ተግባራት በመደገፍ የተሰዳጆችን ቁጥር ለመቀነስ የአዉሮጳ ኅብረት ማለሙ ተሰምቷል። ይህ አካሄድም ለኤርትራና ለምዕራቡ ዓለም አዲስ የግንኙነት በር እንደሚከፍት የሚናገሩ አሉ። ዶቼ ቬለ በዚህ ሳምንት በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ዉይይት አካሂዷል።

ዝርዝሩን ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ