1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የልማት እርዳታና የበርሊኑ ጉባኤ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 3 2001

አንድ መቶ ዘጠና ሁለት አገራትን ወክለው ለተገኙት የጉባኤው ታዳሚያን ታላቅ ፈተና ደቅኖ ነበር። በዋናነት ዓለም የተከሰተባት የፋይናንስ ቀውስ በጉባኤው እንደ እንቅፋት ተጥቅሷል።

https://p.dw.com/p/GDlp
የዶሐው ጉባኤ ታዳሚያን
የዶሐው ጉባኤ ታዳሚያንምስል AP

የልማት እርዳታ ምን መምሰል እንዳለበት ባለፈው ሣምንት የመከረው የዶሐው ጉባኤ ሲጠናቀቅ፤ አንድ መቶ ዘጠና ሁለት አገራትን ወክለው ለተገኙት የጉባኤው ታዳሚያን ታላቅ ፈተና ደቅኖ ነበር። በዋናነት ዓለም የተከሰተባት የፋይናንስ ቀውስ በጉባኤው እንደ እንቅፋት ተጥቅሷል። ከዶሐው ጉባኤ ብዙም ሳይቆይ የልማት ድርጅቶችና ሌሎች ተሳታፊያን የወደፊት የልማት እርዳታን አስመልክቶ አንዳች መፍትሄ ለመፈለግ እዚህ ጀርመን በርሊን ከተማ ውስጥ ተሰብስበው ነበር።