1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የልብና የደም ቧምቧ ጤና

ማክሰኞ፣ የካቲት 4 2006

ብዙዉን ጊዜ አደገኛ ከሚባሉት የጤና ችግሮች ልብና ከልብ ጋ የተገናኙት በዋነኝነት ይጠቀሳሉ። በዓለማችን በአብዛኛዉ ለሞት ከሚያደርሱ የጤና እክሎችም አንዱ በመሆኑም ይታወቃል።

https://p.dw.com/p/1B704
ምስል picture-alliance/chromorange

ይህ የጤና እክል በበለፀጉትና ከፍተኛ ገቢ በሚገኝባቸዉ ሃገራት ከቅርብ ጊዜያት ማለትም ከ1970ዎቹ ወዲህ ገዳይነቱን ለመቀነስ መቻሉ ቢነገርለትም፤ በተቃራኒዉ በድሃ ሃገራት ይህ የጤና እክል እየተስፋፋ መምጣቱንና ብዙዎችንም ለጉዳት እየዳረገ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። የአመጋገብና የአኗኗር ልማድ የተለያዩ የጤና እክሎች ማስከተላቸዉ ቢታወቅም በተለይ ልብ እና የደም ሥሮች በዚህ ለጉዳት መዳረጋቸዉን የህክምና ባለሙያዎች በተደጋጋሚ ያሳስባሉ።

እንዲህ ያለዉ የደም ሥር መደፈንም ይሁን ከአቅም በላይ ተወጥሮ የመፈንዳት ሁኔታ በአብዛኛዉ የስኳር በሽተኞችን እንደሚያጠቃ ዶክተር ያሬድ ተካበ አመልክተዋል። እሳቸዉ እንደሚሉትም ለስኳር ታማሚዎች የሚጎዳዉን የደም ሥር የመተካቱ እድል የለም። ባጠቃላይ አንድን ሰዉ ለልብና የደም ሥር በሽታዎች የሚጋልጠዉ ምንድነዉ ለሚለዉ ጥያቄም፤ በዘርፉ ምርምር ያደረጉት እና የሚያደርጉት ባለሙያ የስኳር በሽታ፤ ከፍተኛ የደም ግፊት፤ በደም ዉስጥ ከፍተና የስብ መጠን መኖር፤ ሲጋራ ማጤስ፣ ጭንቀት፤ ዉፍረት፤ በዘር ወይም በቤተሰብ ችግሩ መኖሩ፤ እድሜ እንዲሁም ፆታ ጭምር እንደሆነ ዘርዝረዋል። ችግሩ ከመከሰቱ አስቀድሞ ለመከላከል ሊደረጉ የሚገባቸዉን በሚመለከት ዶክተር ያሬድ ይመክራሉ።

Darm Schema Medizin
ምስል Fotolia/Sebastian Kaulitzki

ዶክተር ያሬድ ተካበ በተለይ በሳይንሳዊ አጠራሩ አትሮስክሎሮሲስ ስለሚባለዉና የደም ሥር መዘጋት ብሎም ፈንድቶ ከፍተኛ አደጋ ስለሚያስከትለዉ እና ምርምር ስላደረጉበት የጤና ችግር አድማጮቻችን ተረድተዉ ራሳቸዉን ከችግሩ እንዲከላከሉ እንደሚሹ በገለፁልን መሠረት የዛሬ እንግዳችን አድርገናቸዋል።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ