1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የልጅነት ልምሻ «ፖልዮ»ክትባት ዘመቻ

ዓርብ፣ ነሐሴ 8 2007

በተለይ በኢትዮጵያ ከጎረቤት ሃገራት ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች ክትባቱ በሰፊው እየተሰጠ ነው ። ከአንድ ዓመት በፊት የመጨረሻ የተባለው የፖልዮ ተጠቂ በሶማሊያ ከተገኘ በኋላ ክትባቱ በዘመቻ ሲሰጥ ቆይቷል ።

https://p.dw.com/p/1GFjl
Nigeria Polio-Impfung
ምስል Global Polio Eradication Initiative

[No title]

አፍሪቃ ቀንድ የልጅነት ልምሻ ወይም ፖሊዮ እንዳይዛመት የተጠናከረ የክትባት ዘመቻ በመካሄድ ላይ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት በምህፃሩ UNICEF አስታወቀ ። ድርጅቱ እንዳለው በተለይ በኢትዮጵያ ከጎረቤት ሃገራት ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች ክትባቱ በሰፊው እየተሰጠ ነው ። ከአንድ ዓመት በፊት የመጨረሻ የተባለው የፖልዮ ተጠቂ በሶማሊያ ከተገኘ በኋላ ክትባቱ በዘመቻ ሲሰጥ ቆይቷል ። በናይጀሪያም የፖልዮ በሽተኛ ከተገኘ ባለፈው ሀምሌ አንድ ዓመት አለፈ ። ሆኖም አፍሪቃ ከፖልዮ ነፃ ነች ለማለት ተጨማሪ ሁለት ዓመታት መጠበቅ እንዳለበት UNICEF አስታውቋል ።በሽታውን ለሚከላከለው ክትባት መግዣ የአውሮፓ ህብረት እርዳታ መስጠቱን የአዲስ አበባው ወኪላችን ዘግቧል ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ