1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሐዋሳ ነጋዴዎች አቤቱታ

ማክሰኞ፣ ጥር 28 2011

የሐዋሳ ከተማ መስተዳድር የንግድ መደብሮቻቸዉን ያሸገባቸዉ አንድ መቶ ያሕል ነጋዴዎች እርምጃዉን ባደባባይ ሰልፍ ተቃወሙ።ዛሬ ለደቡብ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ፅሕፈት ቤት አቤቱታ ያቀረቡት ነጋዴዎች እንደሚሉት የከተማዉ አስተዳደር መድብሮቻቸዉን የዘጋዉ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3Clwr
Mercato Addis Abeba Äthiopien
ምስል DW/M. Gerth-Niculescu

                    

የሐዋሳ ከተማ መስተዳድር የንግድ መደብሮቻቸዉን ያሸገባቸዉ አንድ መቶ ያሕል ነጋዴዎች እርምጃዉን ባደባባይ ሰልፍ ተቃወሙ።ዛሬ ለደቡብ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ፅሕፈት ቤት አቤቱታ ያቀረቡት ነጋዴዎች እንደሚሉት የከተማዉ አስተዳደር መድብሮቻቸዉን የዘጋዉ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ነዉ። የሐዋሳ መስተዳድር ባለሥልጣናት ግን እርምጃዉ የተወሰደዉ ነጋዴዎቹ ከዚሕ ቀደም የገቡትን ዉል ጥሰዉ የንግድ መደብሮቹን በመያዛቸዉ ነዉ።አቤቱ የቀረበለት የክልሉ ርዕሠ-መስተዳድር ፅሕፈት ቤት በአምስት ቀናት ዉስጥ ለጉዳዩ እልባት ለመስጠት ቃል ገብቷል።

 

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ