1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሐጅ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 25 2009

የቀድሞዉ የጅማ ንጉስ አባ ጅፋር አባ ጎሞል ከአንድ መቶ ዓመት በፊት በመካ ከተማ የገዙት ቤትም 550 ኢትዮጵያዊያን ሀጃጆች በነጻ እንዳረፉበት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/2jA9l
Saudi-Arabien Hadsch in Mekka
ምስል picture-alliance/dpa/SPA

ከስምንት ሺህ በላይ ኢትዮጵያዉያንም ይሳተፋሉ፤

የኢድ አል አድሐ በዓል ነገ በመላዉ ዓለም ይከበራል።ከ 2 ሚሊዮን የሚበልጡ ሙስሊሞች ደግሞ በመካ፣ በመዲና እና በአረፋ ተራራ የሐጅ ስርዓታቸውን እየፈጸሙ ነዉ። ከስምንት ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያንም ለዘንድሮዉ ሐጅ ሳዑዲ ዓረቢያ ገብተዋል፡፡ የቀድሞዉ የጅማ ንጉስ አባ ጅፋር አባ ጎሞል ከአንድ መቶ ዓመት በፊት በመካ ከተማ የገዙት ቤትም 550 ኢትዮጵያዊያን ሀጃጆች በነጻ እንዳረፉበት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት አስታውቀዋል፡፡ ኢትዮጵያዉያን ለሐጅ ጉዞ እያንዳንዳቸው ከ 80 ሺህ ብር በላይ ከፍለዋል፡፡ ተጓዞቹ ያን ያሕል ገንዘብ ከፍለዉ ተገቢዉ መስተንግዶ አልተደረገልንም በማለት የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ይወቅሳሉ። የሪያዱ ወኪላችን ስለሺ ሽብሩ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ስለሺ ሽብሩ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ