1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሔሊኮፕተር አደጋ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 18 2011

ወደ ጂማ ለመብረር ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባዉ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ የተነሳችዉ ባለሁለት ሞተር የግል ኩባንያ ሔሊኮብተር ቦሌ ቡል ቡላ ስትደርስ መኖሪያ ቤቶች ላይ ወድቃለች።

https://p.dw.com/p/3HWHg
Äthiopien l Helicopter bei Addis Abeba verunglückt
ምስል Solomon Muchie

በሰው ላይ ጉዳት አልደረሰም ተብሏል

                           

አዲስ አበባ ከመጋቢት መጀመሪያዉ የአዉሮፕላን አደጋ ሐዘንዋ በቅጡ ሳትፅናና ዛሬ ሌላ የሔሊኮብተር አደጋ አጋጥሟታል።ወደ ጂማ ለመብረር ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባዉ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ የተነሳችዉ ባለሁለት ሞተር የግል ኩባንያ ሔሊኮብተር ቦሌ ቡል ቡላ ስትደርስ መኖሪያ ቤቶች ላይ ወድቃለች።በሕይወትና አካል ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።ንብረት ግን፣ የአካባቢዉ ነዋሪዎች እንደሚሉት ግምቱ በዉል ያልታወቀ ጠፍቷል።

 ሠለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

ተስፋለም ወልደየስ