1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕወሓት አዲስ ጥቃት በአፋር

ረቡዕ፣ ጥቅምት 3 2014

ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ከጥቅምት 1 ቀን፤ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በአፋር ክልል ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ተገለጠ። የአፋር ክልል ባለስልጣናት ለዶይቼ ቬለ እንዳረጋገጡት በአፋር ክልል ዞን አራት፤ እዋ ወረዳ፤ ፈንቲረሱ በምትባል ስፋራ ላይ ባነጣጠረው የከባድ ጦር መሣሪያ ጥቃት የንጹሃን ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ  ተቀጥፏል።

https://p.dw.com/p/41cgx
Äthiopien Spezialeinheiten der Armee und Milizen in der Region Afar
ምስል Seyoum Getu/DW

ጥቃቱ ከጥቅምት 1 ቀን፤ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ነው

ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ከጥቅምት 1 ቀን፤ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በአፋር ክልል ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ተገለጠ። የአፋር ክልል ባለስልጣናት ለዶይቼ ቬለ (DW) እንዳረጋገጡት ከትናንት በስቲያ ሰኞ ጀምሮ በአፋር ክልል ዞን አራት፤ እዋ ወረዳ፤ ፈንቲረሱ በምትባል ስፋራ ላይ ባነጣጠረው የከባድ ጦር መሣሪያ ጥቃት የንጹሃን ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ  ተቀጥፏል። ሕወሓት በአፋር ክልል ከወራት በፊት ተቆጣጥሯቸው የነበረ ስፍራዎችን መልቀቁ የተገለጠ ቢሆንም፤ ጥቃቱን አደረሰ የተባለው በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ሃሮ ከምትባል ስፍራ ከ17-20 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ሆኖ ነው። የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ጠጨማሪውን እንደሚከተለው አጠኛቅሮታል።

ሰኞ ጠዋት ከአራት ሰዓት ገደማ ጀምሮ ሕወሓት ከአፋር ክልል ጭፍራ 30 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ በምትገኘው እዋ ወረዳ ፈንቲረሱ ከተማ አድርሷል በተባለው የከባድ መሣሪያ ጥቃት ጉዳትን ማስከተሉ ተነግሯል። የአፋር ክልል መንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ መሃመድ አህመድ እንደሚሉት ከሰኞ ጀምሮ ትናትም ቀጥሎ ተፈጽሟል በተባለው በዚህው የከባድ ጦር መሣሪያ ጥቃት የ6 እና የ9 ዓመታት ዕድሜ ያላቸው ህጻናትን ጨምሮ የሰባት (7) ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ 15 ሰዎች ላይ ደግሞ አስከፊ የተባለ ጉዳት መድረሱም ተጠቅሷል። ከ20 ኪ.ሜ ርቀት በሕወሓት ተተኩሷል የተባሉት ከባድ የጦር መሣሪያ ብዛት እና አነጣጥሮ ስላረፈባቸውም ስፋራ የተጠየቁት አቶ መሃመድ አህምድ ሰላማዊ ሰዎች እጅግ በአሰቃቂ ሁኔታ በጥቃቱ መገደላቸውን ተናግረዋል።ንጹሃን ዜጎችን ከጦርነቱ ቀጠና ስለማንቀሳቀስ እና ከለላ መስጠትም የተጠየቁት የአፋር ክልል ባለስጣን አቶ መሃመድ፣ ጥቃቱ ሆን ብሎ በንጹሃን ላይ ማነጣጠሩን ገልጸው ሞግተዋል። በአከባቢው ላይ ጦርነቱ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄ መሆኑ ተጠቁሟል። በቴሌኮሚዩኒኬሽን ግንኙነት መቋረጥ ምክኒያት ስለ አፋሩ ጥቃት ከህወኃት ወገን ማጣራት አልተቻለም። የሕወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ሰኞ እለት በየአቅጣጫ የተቀናጀ ጦርነት ያሉት በሰራዊታቸው ላይ መከፈቱን ለሮይተርስ የዜና ወኪል መግለጻቸው ይታወሳል።   

Äthiopien Spezialeinheiten der Armee und Milizen in der Region Afar
ምስል Seyoum Getu/DW

ሥዩም ጌቱ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ