1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሳይንስ

የሕዋ ቴክኒዎሎጂ ብሔራዊ ፖሊሲ በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 9 2011

ኢትዮጵያ በ2012 ዓም ጥቅምት ወር ላይ ሳተላይት እንደምታመጥቅ የኢትዮጵያ ሕዋ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ተቋም አስታወቀ። የሕዋ ቴክኖሎጂ ብሔራዊ ፖሊሲን ተግባራዊ ለማድረግ በተዘጋጅ የግንዛቤ መስጫ ውይይት ላይ እንደተገለጸው ኢትዮጵያ በሚቀተለው ዓመት ሳተላይት ለማምጠቅ የሳተላይት ግንባታ በኢትዮጵያዉያን እና ቻይናውያን ባለሙያዎች እያከናወነች ነው።

https://p.dw.com/p/3GzKV
Äthiopien Bahir Dar - Treffen zu Raumfahrt:  Solomon Belay Leiter des Ethiopian Space science and technology Institute
ምስል DW/A. Mekonnen

«በሚቀጥለው ዓመት ሳተላይት ታመጥቃለች»

 የስፔስ ሳይንስ ባለሙያና በኢትዮጵያ የጠፈር ሳይንስ ማኅበረሰብ የአማራ ክልል ሰብሳቢ ዶክተር ፀጋዬ ካሳ እንዳሉት አገራችን በሚቀጥለው ኣመት ሳተላት ወደ ህዋ ታመትቃለች። ሳተላይት በሕዋ ውስጥ የመቆያ ጊዜው ውስን ሰለሆነ ከዚያ በኋላ ኢትዮጵያውያን  ባለሙያዎች በራሳቸው የሳተላይት ግንባታ በተከታታይ እንዲከናውኑ ይደረጋልም ብለዋል። የኢትዮጵያ ሳተላይት በቀጣዩ ዓመት ቻይና ላይ ወደ ሕዋ እንደምትመጥቅና ዋና ዓላማዋ የኮሙዩኒኬሽን ተግባራትን ማከናወን ነው ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ የጠፈር ሳይንስ ቴክኖሎጂ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን በላይ በቀጣ ሊከናወኑ የታሰቡ ተግባራትን በመዘርዘር፤ ዘርፉን ለማጠናከር የባለሙዎችን አቅም በተለያዩ መንገዶች ለመገንባትም እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ የጠፈር ሳይንስ እንቅስቃሴ የተጀመረው በጎርጎርዮሳዊው የዘመን ቀመር በ19950ዎቹ ቢሆንም ትኩረት አግኝቶ በዘርፉ ጉልህ ሥራ መሥራት የተጀመረው ግን በ2004ዓ,ም ነው።
ዓለምነው መኮንን 

Äthiopien Bahir Dar - Treffen zu Raumfahrt
ምስል DW/A. Mekonnen

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ