1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕገ ወጥ ስደተኞች ጉዳይ በኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ የካቲት 25 2013

የስደተኛዉን ቁጥር ለመቀነስ በየጊዜዉ የሚወጡ ደንቦችና የሚደረጉ ዉይይቶች በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያንን በተለይም ወጣቱን ወደ አዉሮጳ፣ አሜሪካና መካከለኛዉ ምሥራቅ አንጋጥጦ እንዲመለከት ከማድረግ አላገዱትም

https://p.dw.com/p/3qDcR
Jemen afrikanische Migranten in Harad
ምስል DW/Alsoofi

ኢትዮጵያ፣ ሕገ ወጥ ስደትና መፍትሔዉ

   

ከኢትዮጵያ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ተለያዩ ሐገራት የሚሰደደዉ፣ ለመሰደድ ሲሞክር በየበረሐዉና ባሕር ዉስጥ የሚሞተዉ፣ በሰዉ አሸጋጋሪዎችና ወሮበሎች የሚገደለዉና የሚሰቃየዉ ኢትዮጵያዊ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነዉ።የስደተኛዉን ቁጥር ለመቀነስ በየጊዜዉ የሚወጡ ደንቦችና የሚደረጉ ዉይይቶች በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያንን በተለይም ወጣቱን ወደ አዉሮጳ፣ አሜሪካና መካከለኛዉ ምሥራቅ አንጋጥጦ እንዲመለከት ከማድረግ አላገዱትም።የሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ በጉዳዩ ላይ እንዲነጋገሩ የጋበዛቸዉ ባለሙያዎችና አጥኚዎች ችግሩን ለማቃለል አሁንም የመንግስት ጠንካራ ርምጃ አስፈላጊ ነዉ ይላሉ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ