1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሕፃናት ስደተኞች መከራ

ማክሰኞ፣ መስከረም 3 2009

ዓለም አቀፉ የሕፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ባለፈዉ ሳምንት ባወጣዉ ዘገባዉ እንዳስታወቀዉ ጦርነት፤ጭቆናና ችግር ከጠናባቸዉ ሐገራት ከ28 ሚሊዮን የሚበልጡ ሕፃናትና ልጆች ተሰድደዋል።

https://p.dw.com/p/1K1Qt
ምስል picture-alliance/dpa/K. Nietfeld

ጦርነት፤ጭቆና፤በደልና ችግርን ሽሽት ከየሐገሩ ከሚሰደደዉ ሕዝብ መካከል ግማሽ ያሕሉ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችና ሕፃናት መሆናቸዉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።ዓለም አቀፉ የሕፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ባለፈዉ ሳምንት ባወጣዉ ዘገባዉ እንዳስታወቀዉ ጦርነት፤ጭቆናና ችግር ከጠናባቸዉ ሐገራት ከ28 ሚሊዮን የሚበልጡ ሕፃናትና ልጆች ተሰድደዋል።በዘገባዉ መሠረት አብዛኞቹ ሥደተኛ ልጆችና ሕፃናት የተሰደዱት ካለወላጅ ወይም አሳዳጊ በሞሆኑ በየደረሱበት ለባርነት፤ ለወሲብ ንግድና ለወንጀል ይዳረጋሉ።ጊዮርግ ሽቫርተ የዘገበዉን ይልማ ኃይለሚካኤል አጠናክሮታል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ