1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመማሪያ መፅሐፍት እጥረት በኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ መጋቢት 15 2003

የኢትዮጵያ መንግሥት አዲስ ለቀየሰዉ የትምሕርት መርሕ ማስፈፀሚያ የተዘጋጁ የማስመተማሪያ መፅሐፍት በወቅቱ ለየትምሕርት ቤቶቹ አለመድረስ የመማር ማስተማሩን ሒደት እንዳጎለዉ አንዳድ የደቡብ ኢትዮጵያ ተማሪዎችና አስተማሪዎች አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/RCGY
ተማሪዎችምስል DW

በተለይ በቅርቡ የሚሰጠዉን የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችና አስተማሪዎቻቸዉ፥የመፅሐፍቱ መዘግየት የተማሪዎቹን ዉጤት ይጎዳዋል ብለዉ ይሰጋሉ።የደቡብ መስተዳድር እና የፌደራላዊዉ የትምሕርት ጉዳይ ባለሥልጣናት እንደሚሉት ግን ተማሪዎቹንም ሆነ አስተማሪዎቻቸዉን ብዙ የሚያሰጋ ነገር የለም።ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ተጉዞ የነበረዉ ታደሰ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ታደሰ እንግዳዉ

ነጋሽ መሀመድ

አርያም ተክሌ