1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመስቀል በአል አከባበር ባህል

ሐሙስ፣ መስከረም 18 2004

እዩት እዝያ ላይ የግራሩን መንታ፣ አይንሽ ያበራል እንደ ሎሚታ ከሎሚታዉስ ያንቺ አይን ይበልጣል፣ እንደመስታወት ከሩቅ ያበራል። ካንቺማ ወዳጅ ይሻላል ትል፣ አጥር ላይ ዘምቶ ያገለግል። ካንቺማ ወዳጅ ይሻላል ዱባ፣ አጥር ላይ ዘምቶ ያደምቃል አንባ። እዮሃ እዪሃ አደራ ደመራ፣ አደራ መስቀሎ ጥባ ጥባ ቶሎ!

https://p.dw.com/p/RoO4
የደመራ በአል በፍራንክፈርት ከተማምስል DW

በገጠሩ ከዘመን መለወጫ በአል በኋላ የመስቀል በአል እስኪ ደርስ ድረስ ወጣት ወንድና እና ሴቶች በግጥም መልክ እየተቀባበሉ እንዲህ ያዜማሉ። እንኳን ለመስቀል በአል አደረሳችሁ! በጎጃም በጎንደር አካባቢ በመስቀል በአል፣ አንጎሮጎባሽ በያመጡ ያምጣሽ እንደሚባል በአዲስ አበባ የፎክሎር ትምህርት መምህራን በለቱ ዝግጅታችን በስፋት ትንተና ሰጥተዉናል። ልጃገረዶች የመስቀል በአል ከመድረሱ በፊት ነሃሴ ዉስጥ የአሸንዳን ወይም የሻደይን በአል አስታከዉ እስከ መስቀል ድረስ ማታ ማታ ሰባስበዉ በመንደር እየዞሩ ይጨፍራሉ፣ ያዜማሉ።
አያማሩ ደሴ ናዉጣ ከገብሴ፣ ለምን እወጣለሁ እጎጠጉጣለሁ፣ ሄኔታ ሲሞቱ አጥብቄ ሮጣሉ። ሸንበቆና ሸንበቆ፣ ሲወጣ አየሁ ተጣብቆ፣ አትንጫጩ ልጆቼ፣ እመጣለሁ ሰንብቼ ቋንጣ በለስ በልቼ ቋንጣ በለስ ይሉሻል፣ ይኸዉና ቅጠሉ፣ ቀጥቅጭና ቅመሽዉ ወረታዉን ከቻልሽዉ፣ ለዚህ ለዚህ ወረታ፣ አልጋ ሰርቶ መኝታ፣ መሪት ወርዶ ጫጫታ።
እዮሃ እዪሃ አደራ ደመራ፣ አደራ መስቀሎ ጥባ ጥባ ቶሎ! ወጣቶቹ የተሰጣቸዉን ተቀብለዉ፣ የንብ አዉራ ሶነግ፣ የንብ አዉራ ሶነግ፣ የወለዱት ይደግ፣ የወለዱርት ይደግ፣ ብለዉ መርቀዉ ወደ ቀጣዩ ቤት ለጭፈራ፣ ስጦታን ለመቀበል ይሄዳሉ። የመስቀል በአል ባህላዊ አከባበርን በተመለከተ በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ የፎልክሎር ትምህርት መምህር ከአቶ መስፍን መሰለ እና በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ በኢትዮጽያ ቋንቋዎች እና ባህሎች አካዳሚ የጥንታዊ የግዕዝ ጽሁፍ ተመራማሪ መምህር ታደሰ እሱባለዉን አነጋግረን ይዘናል። ሙሉዉን ዝግጅት ያድምጡ


አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ