1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመቀሌ የውሃ ችግር

ዓርብ፣ ኅዳር 17 2003

መቀሌ ውሃ ተጠማች። ነዋሪው ያማርራል። የከተማዋ የውሃ አገልግሎት እየሰራሁ ነው ይላል።

https://p.dw.com/p/QJTZ
የመቀሌ የውሃ ችግር
ምስል picture-alliance/dpa

አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ለዶቸቬሌ እንደገለፁት ውሃ ለማውጣት የሚነደፉ ፕሮጀክቶች ችግሮች ያሉባቸው፤ የከተማዋን የውሃ እጥረት የማቃለል አቅም የላቸውም። ዮሃንስ ገብረእግዚያብሄር እንደዘገበው ከሆነ 100 ሚሊዮን ብር የወጣበትና ለ30 ዓመታት ያገለግላል የተባለው ፕሮጀክት ሁለት ዓመትም አገልግሎት ሳይሰጥ ቆሟል። ፕሮጀክቱን በወሰደው ተቋራጭና በወቅቱ ፕሮጀክቱን በሰጡት የመንግስት ሃላፊዎች መሃል በተፈጠረው ሽኩቻ ፕሮጀክቱ እንደታሰበለት አልሆነም። መቀሌን ከውሃ ጥማት ሊታደጋትም አልቻለም። ከመቀሌ ሌላ ችግሩ በአክሱምና በሽሬ እንደስላሴም የተከሰተ መሆኑን ነው ዮሀንስ ገብረእግዚያብሄር የዘገበው።

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ