1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመንና ፀረ አል ቃይዳ ዘመቻ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 5 2006

በየመን መንግሥት እና በዐረቡ ልሳነ ምድር በሚንቀሳቀው ፣ በምሕፃሩ «ኤ ኪው ኤ ፒ» በሚል መጠሪያ በሚታወቀው የአል ቃይዳ ክንፍ ዓማፅያን መካከል በምሥራቃዊው የሀገሪቱ አካባቢ በተለይ በማሪብ እና በአል ባይዳ ግዛቶች ውዝግቡ ከተባባሰ ካለፉት ጥቂት ጊዚያት ወዲህ የሀገሪቱ መንግሥት ቡድኑን ለመደምሰስ ዘመቻውን አጠናከረ።

https://p.dw.com/p/1Bz5F
ምስል Reuters

በዚሁ መሠረትም በትናንቱ ዕለት በዩኤስ አሜሪካ አብራሪ የለሽ የጦር አይሮፕላን በአል ሁሱን መንደር አቅራቢያ በጣለው ጥቃት በአንድ ተሽከርካሪ ይጓዙ የነበሩ ስድስት የቡድኑን አባላት መግደሉን አስታውቋል። ዓማፅያኑ ቡድኖችም በአፀፋው ጥቃታቸውን ቀጥለው አምሥት ወታደሮችን ገድለዋል። በየመን በ«ኤ ኪው ኤ ፒ» አንፃር ስለተጀመረው ዘመቻ እና ስለዓማፅያኑ እንቅስቃሴ ሰንዓ ያለውን ወኪላችንን ግሩም ተክለሀይማኖት አነጋግሬው ነበር።

ግሩም ተክለሀይማኖት

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ