1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመንን ሥጋት ላይ የጣለዉ የኮሌራ ወረሽኝ

ዓርብ፣ ሐምሌ 14 2009

በየመን የተቀሰቀሰው የኮሌራ ወረርሽኝ ወደ 300 ሺህ ሰዎችን መግደሉን የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት ባለፉት ሳምንታት አስታዉቋል።  የዓለም የጤና ድርጅት በበኩሉ በኮሌራ ተይዘዋል በሚል የሚጠረጠሩ 307 ሺህ ዜጎች መመዝገባቸዉን አመልክቷል። 

https://p.dw.com/p/2gz5N
Cholera  Jemen
ምስል picture alliance/dpa

MMT Q&A Saudi Amnesty and Ethiopian - MP3-Stereo

ሥርጭቱን ለመግታት አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደም በሽታዉ ባጭር ጊዜ ዉስጥ ከሩብ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ሊለክፍ እንደሚችል ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። ሳዑዲ አረቢያ መራሹ የአረብ ሃገራት ጦር የመንን መደብደብ ከጀመረ ከካቻምና መጋቢት ወር ጀምሮ የተባባሰዉ ጦርነት ከ8 ሺህ በላይ ሕዝብን ፈጅቷል፤ ከ 45 ሺህ ሕዝብ በላይ ደግሞ አቁስሏል። ሰንዓ የሚገኘዉ ተባባሪ ዘጋቢ ግሩም ተክለሃይማኖት እንደገለፀልን ደግሞ ከኮሌራ ወረርሽኝ በሽታ በተጨማሪ ሰሞኑን በሀገሪቱ የዓይን ሕመም እየተሰራጨ ነዉ። አዜብ ታደሰ ስለጉዳዩ ግሩምን ቀደም ብላ በስልክ አነጋግራዉ ነበር።

ግሩም ተክለ ሃይማኖት

አዜብ ታደሰ