1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመአከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ምርጫ

Merga Yonas Bulaዓርብ፣ ታኅሣሥ 29 2008

ሁለት የቀድሞ የማዕከላዊ አፍሪቃ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ፣ ማለትም አንሴት-ጅኦርጅስ ዶሎጉሌ እና ፋዉስትን አርቻንጌ ቶዉዴራ፣ ባለፈዉ ሳምንት የተካሄደዉ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቀዳሚዎቹን ሥፍራዎች ይዘዋል።

https://p.dw.com/p/1HaTb
Zentralafrikanische Republik Bangui Wahlen Wahllokal
ምስል picture-alliance/AP Photo/H. Diaspora

[No title]

ከ30 በላይ ፖለቲከኞች ለፕሬዝዴንትነት የተወዳደሩ ሲሆን፤ 20 የምሆኑ እጩዎች የድምፅ ቆጠራዉ ለጊዜዉ እንድቆም ቢጠይቁም፣ መንግስት በበኩሉ ጥያቄያቸዉን እንደማይቀበል እና ቁጠራዉ እንደምቀጥል አስታዉቋል።

ሁለት ሚሊዮን የሞሆን ሕዝብ ድምፅ የሰጠበት ይህ ምርጫ ለዓመታት እየተካሄዴ ያለዉን የእርስ በእርስ ጦርነት ለማስቆም ይረዳል ተብሎ ይታመናል።ድምፅ ከተሰጠ በኋላ የተነሳዉ ዉዝግብ ግን ምርጫዉ እንደታሰበዉ ሊሆን እንዳልቻለ ዘገባዎች ያሳያሉ። በተለይም በ1000 የድምፅ ብልጫ እየመሩ ያሉት ቶዉዴራ እና ዶሎጉሌ እርስ በእርስ መካሰስ ተስፋዉን ጨርሶ እንዳያጠፋዉ አስቷል።በሁለቱ መካሰስ ጀርባ ያለዉን ጉዳይ አስመልክቶ በቻታም ሃዉስ የአፍርቃ ክፍል ተመራማር የሆኑት ፖል ሜሌ ለዶቼ ቬሌ ስናገሩ፣ <<እኔ የማስበዉ ይህ ሁኔታ የተወሰኑ እጩዎች የተሻለ ነገር ለማድረግ የሚጥሩ፣ ስለ ምርጫዉ አካሄድ ሊጠይቁ የሚችሉት ግዜ ለመግዛት ልሆን ይችላል። ምክንያቱም የአለማቀፍ ህብረተሰብ በ ማይከላዊ አፍርቃ ያላቸዉን አመለካከት ምርጫዉ በጥሩ መልክ እንደተካሄዴ እና ብዙዎቹ እጩዎች አሁን የምርጫዉ እደት እያጠየቁ ያሉት የራሳቸዉን ታዘብዎች ላመላክም አለተጨነቁም፣ ምክንያቱም እራሳቸዉ ብዙ እንሰራለን ብሎ ስላልጠበቁ ነዉ።>>

Zentralafrikanische Republik - Anicet Georges Doleguele
ምስል Getty Images/AFP/I. Sanogo

እናም የፖለትካ አካሄዱን አያወሰስብም ይሉታል ተብሎ ፖል ሜሌ ሲጠየቁ፣ <<በጣም ተገርሜያለዉ። ለምርጫዉ ወጥቶ የመጡት ቁጥራቸዉ በጣም ብዙ ነበር እናም ለሁለቱ ዋና እጩዎች የተሰጠዉ ድምፅ ብዙ ድጋፍ እንዳገኙ ነዉ የሚያሳየዉ። ሌሎች ከሶስተኛ እስከ አምስተኛ ደረጃ ላይ የምገኙት ከሁላቱ እጩዎች በጣም ያነሰ እና ቶዉዴራ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር እና ዶሎጉሌ፣ የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ እየመሩ ያሉትን ደረጃ ለመድረስ ብዙ ያስፈልጋቸዋል።>>


የምርጫዉ ዉጤት ሙሉ በሙሉ ቢነገር ሊያመጣ የሚችለ,ዉን የፖለቲካ ዉጥረት አስመልክቶ ፖል ሜሌ ለዶቼ ቬሌ ሲናገሩ ብዙም ዉጥረት እንደማይጠብቁ፣ ምክንያቱም ላለፉት ሶስት ዓመታት ማይከላዊ አፍርቃን ይዞ የነበሩት ችግሮች በቀጥታ ከዋና ፖለቲካ ሃይሎች ጋር ስላልተያያዘ ነዉ ይላሉ። ለዚህም ነዉ አሁን በምርጫ ግዜ የሚፈጠሩት የፖለቲካ ችግሮች ወደ መሳርያ ግጭት ይወስደዋል የሚል እምነት የለኝም ይላሉ በለሙያዉ።

Faustin Archange Touadera Ex-Premier Zentralafrikanische Republik
ምስል Getty Images/AFP/S. Kambou

ባለፈዉ ሳምንት የተካሄዴዉ ምርጫ ተስፋ እንደተደረገ ሊሆን ባይችልም የሽግግር መንግስት ወይም የምርጫ ኮሚሽን ወይም የአለማቀፉ ህብረተሰብ ተሰፋ የምያደርጉት የመጀመርያ ምርጫ ዙር ሁለት መርዎችን እንደምያወጣ ነዉ። ሁለቱም እጩዎች መንግስት መስርቶ ለመምራት ጠንካራ ልምዶች አሏቸዉ ግን መጨረሻ ላይ አንድ እጩ ለፕሬዚዴንቲነት እንደምመረጥ ይጠበቃል።


ሴሌካ ተብሎ የሚጠራዉ የቀድሞዉ አማፂ ቡድን ማዕከላዊ አፍሪቃን ከተቆጣጠረ ማግሥት፤ ሴሌካን በመዋወም በተነሱ ክርስቲያን ሚሊሺያዎችና በሙስሊም ታጣቂዎች በመካከል በተፈጠረ ግጭት በሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ተገድሏል።በሚሊዮን የሚቆጠር ተሰድዷል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሃመድ