1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመካከለኛዉ ምሥራቅ ሠላምና የአሜሪካዉ መልዕክተኛ

ማክሰኞ፣ መስከረም 5 2002

የጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔትንያሁ መንግሥት በፍልስጤም ግዛቶች ላይ የሠፈራ መንደር ማስገንባቱን እንዲያቆም የሚቀርብለትን ጥያቄ አለመቀበሉ የሰላም ድርድሩን ተስፋ እንዳያጨናጉለዉ አስግቷል

https://p.dw.com/p/JhJB

የተስተጓጎለዉ የእስራኤልና የፍልስጤም የሠላም ድርድር እንዲያንሰራራ የሚጥሩት የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልዕክተኛ ጆርጅ ሚቼል ዛሬ የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁን እየሩሳሌም ዉስጥ አነጋግረዋል። ማምሻቸዉን ደግሞ የፍልስጥሙን ፕሬዝዳት ማሕሙድ አባስን ለማነጋገር ወደ ረመላሕ ይሔዳሉ።የሚቼል ያሁኑ ተልዕኮ ሁለቱ መሪዎች ከፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ ጋር በቅርቡ ኒዮርክ ያደርጉታል የተባለዉን ጉባኤ ለማመቻቸት ነዉ።የጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔትንያሁ መንግሥት በፍልስጤም ግዛቶች ላይ የሠፈራ መንደር ማስገንባቱን እንዲያቆም የሚቀርብለትን ጥያቄ አለመቀበሉ የሰላም ድርድሩን ተስፋ እንዳያጨናጉለዉ አስግቷል።የየሩሳሌሙ ወኪላችን ዜናነሕ መኮንን ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።z

ዜናነሕ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ