1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመካከለኛው አፍሪቃ ሪፐብሊክ ቀውስ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 15 2006

የተቀሰቀሰው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ካልተደረገ ሀገሪቱ ወደ አስከፊ የእርስ በእርስ ጦርነት ልታመራ የምትችል መሆኑን በርካታ የዓለም ዓቀፍ የሠብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶችና የመንግሥታቱ ድርጅት ጽ/ቤት በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው።

https://p.dw.com/p/1AgVm
ምስል PHILIPPE HUGUEN/AFP/Getty Images

በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ የተቀሰቀሰው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ካልተደረገ ሀገሪቱ ወደ አስከፊ የእርስ በእርስ ጦርነት ልታመራ የምትችል መሆኑን በርካታ የዓለም ዓቀፍ የሠብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶችና የመንግሥታቱ ድርጅት ጽ/ቤት በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው። በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ በተከሰተው የጎሣና የኃይማኖት ግጭት ሰበብ እስካሁን ከ 1000 በላይ ሰዎች መገደላቸው፣ ከ700 000 በላይ መፈናቀላቸው እና ከ40 000 በላይ ደግሞ ወደ ጎረቤት ሃገራት መሰደዳቸውን የተመድ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት አስታውቋል። ፈረንሣይ በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ የተከሰተውን አለመረጋጋት ለማስወገድ ወታደሮቿን አስቀድማ ብትልክም፤ ከአውሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት የጠበቀችውን ድጋፍ እንዳላገኘች እየተገለፀ ነው። ሰሞኑን ብራስልስ ውስጥ የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ጉዳይ ላይ በመከረው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ተገኝቶ የነበረው የብራስልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሤ የሚከተለውን ዘገባ ከብራሰልስ ልኮልናል።

ገበያው ንጉሤ
ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ