1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመጀመሪያ የህክምና ርዳታ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 5 2006

የመጀመሪያ የህክምና ርዳታ ሰዎች በየትኛዉም አጋጣሚ የሚደርስባቸዉ አደጋ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል የሚሰጥ ጊዜያዊ ርዳታ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1BzDR
Erste Hilfe Kurs
ምስል Bilderbox

ሰዎች አደጋ ሲያጋጥም ወደሃኪም ቤት ሄደዉ ተገቢዉ የህክምና አገልግሎት እስኪደረግላቸዉ ድረስ በቦታዉ ሊያገኙት የሚችለዉ ርዳታ የመጀመሪያ የህክምና ርዳታ ነዉ። የመጀመሪያ የህክምና ርዳታ የተባለዉም ከሃኪም የሚገኘዉን ተገቢና ሙያዊ የህክምና ርዳታ እንደማይተካ ለማመላከት ነዉ። የመጀመሪያ የህክምና ርዳታ በተለያዩ አደጋዎች የተጎዱ ወገኖች ሃኪም ቤት እስኪደርሱ ለመርዳት የሚያስችል ዓለም ዓቀፍ ይዘት ያለዉ የህክምና ርዳታ ነዉ። ይህን ርዳታ መስጠት የሚችሉ ሰዎች ደግሞ ራሳቸዉ አስቀድመዉ ተገቢዉን ስልጠና ሊወስዱ ይገባል። ይህን ስልጠና በመስጠት ከሚታወቁ ተቋማት አንዱ ቀይ መስቀል ነዉ። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በየክልሉ 11 ቅርንጫፎች እና 32 የዞን ቅርንጫፎች ከ3500 በላይም ኮሚቴዎች እንዳሉት ነዉ አቶ በቃሉ አያሌዉ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ገልጸዋል። ሰፊ መዋቅር አለዉ እንዳለዉ ያመለከቱት ይህ ማኅበር ባለበት አካባቢም በቀይ መስቀል የሰለጠኑ ወጣቶች ድጋፍ እንደሚያደርጉ በመጠቆምም ያ ግን በቂ ነዉ ብለዉ እንደማያምኑ ዘርዝረዋል። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ለበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ብቻ ሳይሆን ለፋብሪካዎችንም ሆነ ለአንዳንድ ድርጅቶች የመጀመሪያ የህክምና ርዳታ ስልጠና እንደሚሰጥናም አስረድተዋል። አንጋፋዉ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበርም ለበርካታ ዓመታት ባደረገዉ እንቅስቃሴ በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ስልጠናን እንዲወስዱ ማድረጉን ገልጸዋል። እንዲያም ሆኖ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የስልጠና መርሃግብሩን ለማስፋት የአቅም ዉሱንነት መኖሩን አልሸሸጉም።

Symbolbild Afghanistan - Rotes Kreuz
ምስል picture-alliance/Ton Koene

ሙሉዉን ዝግጅት ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ