1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የስፖርት ዝግጅት

ሰኞ፣ መጋቢት 16 2011

ከሁለት አመት የወሊድ እረፍት በኋላ ወደ ውድድር የተመለሰችው  ኬንያዊት አትሌት ፕሪስካ ጂፕቶ 1፡08፡26 በመግባት ቀዳሚ ስትሆን ፥መሰረት መልካ 1፡10፡39 ሰከንድ በመጨረስ ሁለተኛ ሆናለች ሌላዋ ኪንያዊት አትሊት ሙርጊ ዋመቡኢ ደግሞ ሶስተኛ ሆናለች።

https://p.dw.com/p/3FeBs
Fußball Champions League l Paris St Germain v Manchester United | Jubel (1-3)
ምስል Imago/R. Hart

የስፖርት ጥንቅር፤ መጋቢት 16 ቀን 2011 ዓ.ም

ትላንት በሚላን በተካሂደው የግማሽ ማራቶን ውድድር በ ሁለቱም ፆታ ኬንያውያን አትሌትች አሽናፊ ሆነዋል በሞቃታማ አየር በተካሄደው የትንንቱ ውድድር ኢትዮጵያዊትዋ አትሊት መሰረት መልካ አስቀድማ መሪነቱን ይዛ ነበር ፥ ከሁለት አመት የወሊድ እረፍት በኋላ ወደ ውድድር የተመለሰችው  ኬንያዊት አትሌት ፕሪስካ ጂፕቶ 1፡08፡26 በመግባት ቀዳሚ ስትሆን ፥መሰረት መልካ 1፡10፡39 ሰከንድ በመጨረስ ሁለተኛ ሆናለች ሌላዋ ኪንያዊት አትሊት ሙርጊ ዋመቡኢ ደግሞ ሶስተኛ ሆናለች።በተመሳሳይ በተካሄደው  የወንዶች ውድድር  ኬንያውያን አትሊቶች ከ1 እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ አሽናፊ ሆነዋል። የፊታችን ቅዳሚ በዴንማርክ ለሚካሂደው የ ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮን ውድድር 582 ታዋቂ አትሊቶች ከ 67 ሀገሮች ተሳታፊ እንደሚ ሆኑ የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፊዲሪሽን ትናንት አስታውቀዋል። በዚህ ውድድር  14 ኢትዮጵያውያን ወንድ እና 14 ሴት አትሊቶች በአዋቂና በ ከ20 አመት በታች በሚደረገው ውድድር ተሳታፊ እንደሚሆኑ የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፊዲሪሽን ያወጣው ዝርዝር ያሳያል ።በሁለቱም ፆታ በነጠላ አሽናፊው ቀዳሚ የሚሆኑ ት አትሊቶች 30•000  የአሚሪካ ዶላር ሽልማት ያገኛሉ። በዚህ ውድድር ከ 1 -6ኛ የሚወጡ አትሊቶች እያንዳንዳቸው የገንዘብ ሽልማት ሲኖራቸው ሽልማቱ የሚሰጠው አትሊቶች ከአበረታች ንጥረ ነገር ምርመራ ነፃ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ ነው።

አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ

ለ አፍሪካ ዋንጫ ፍልሚያ ያለፍት 24 ሀገሮች በሳምንቱ መጨረሻ በተደረጉት ጨዋታዎች ተለይተዋል ።በመጭው ሰኔ እና ሀምሊ ወር ላይ ለሚካሂደው የዘ ንድሮ የአፍሪካ ሀገሮች  ዋንጫ ውድድር ለማለፍ በየምድባቸው የመጨረሿ የማጧሪያ ውድድር ትላንት እና ካትላንት በስቲያ ቅዳሚና አርብ በተለያዪ ሀገራት ተካሂደዋል።በ ንጉስ ሉዊስ ርወጋሶር ስታድየም በተደረጋው በዚህ ጨዋታ ብሩንዲ በታሪክዋ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ሀለፊ ሆናለች።ግብፅ ለምታስተናግደው የዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ አቻ መውጣት ብቻ የሚጠበቅበት የብሩንዲ ብሔራዊ ቡድን ከትናንት በስቲያ ቅዳሚ ከጋቦን ብሔራዊ ቡድን ጋር ባደረገችው ጨዋታ 1ለ 1 በመለያየት ከምድብ ሥስት አስቀድማ ማለፍዋን ያረጋገጠችውን ማሊን ተከትላ ሁለተኛ በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪቃ ዋንጫ ጨዋታ ኃላፊ ሆናለች ።

ሃና ደምሴ 

ኂሩት መለሰ