1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመጥፋት ስጋት የተደቀነበት ብርቅየው የኢትዮጵያ የዛፍ ዓይነት የዕብ

ሐሙስ፣ ኅዳር 10 2002

በኢትዮጵያ ብቻ ከሚገኙት ዛፎች መካከል አንዱ የሆነው በሳይንሳዊ መጠሪያው ኮርዴዮ ኤዱሊስ፡ ሶማሌዎች ደግሞ የዕብ የሚሉት ዛፍ ካለፉት ጥቂት ጊዚያት ወዲህ በብዛት እየተቆረጠ ብርቱ የመጥፋት ስጋት ተደቅኖበታል።

https://p.dw.com/p/KaD1
ምስል picture-alliance/dpa

ይኸው በሶማል ክልል በዋርዴ ዞን፡ ቡኽ ወረዳ የሚገኘው ብርቅየ ዛፍ ፍሬው በምግብነት፡ ቅጠሉ ለከብቶችና ለግመሎች በመኖነት፡ ግንዱ ደግሞ ለህንጻ ግንባታና ለማገዶ ያገለግላል። ከአስር ዓመታት በፊት በመቶ ካሬ ኪሎሜትር ላይ ይገኝ የነበረው የዕብ ዛፍ በአሁኑ ጊዜ በሀያ ሁለት ካሬ ኪሎሜትር ስፋት ላይ ብቻ እንደሚገኝ ተመራማሪዎች ገልጸዋል። ዩሀንስ ገብረእግዚአብሄር