1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሙስሊም ኮሚቴ አባላት የፍርድ ቤት ውሎ

ረቡዕ፣ ሰኔ 24 2007

ነገ ከሚጠበቀው ብይን ሌላ ፍርድ ቤቱ ቀሪ የምስክሮች ቃል የሰነድ የድምፅና የምስል ማስረጃዎችም እንደሚቀርቡለት ዮሐንስ ዘግቧል።

https://p.dw.com/p/1FrN5
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

[No title]



የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4 ተኛ ወንጀል ችሎት በእነ አቡበከር አህመድ መዝገብ በተከሰሱ 18 የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ነገ ብይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎው ተከሳሶቹ የቀረበባቸውን ክስና የምስክርነት ቃልን በንባብ ካዳመጠ በኋላ የመጨረሻውን ፍርድ ለነገ ማስተላለፉን ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘግቧል። ነገ ከሚጠበቀው ብይን ሌላ ፍርድ ቤቱ ቀሪ የምስክሮች ቃል የሰነድ የድምፅና የምስል ማስረጃዎችም እንደሚቀርቡለት ዮሐንስ ዘግቧል። ተከሳሾቹ ከታሰሩ ሶስት ዓመት ተገባዷል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ