1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሙንሽኑ ገንዘብ አሳታሚ ድርጅት እና ከሙጋቤ ጋር ያለዉ ልዩ ወዳጅነት

ቅዳሜ፣ መጋቢት 20 2000

በመጭዉ የሳምንት መጠናቀቅያ ላይ ዝንባቤዌ የፕሪዝደንት ምርጫ ታካሂዳለች። ለሙጋቤም የቀድሞዉ የአገሪትዋ የገንዘብ ሚኒስቴር Simba Makoni ታላቅ ተፎካካሪ ሆነዉባቸዋል።

https://p.dw.com/p/E0ZD
ሙጋቤ ለአገሪትዋ ወታደሮች እንዲሁም ለገዢዉ መደብ ታማኝ ለሆኑ አስተማሪዎች የደምወዝ ጭማሪ አድርገዋል
ሙጋቤ ለአገሪትዋ ወታደሮች እንዲሁም ለገዢዉ መደብ ታማኝ ለሆኑ አስተማሪዎች የደምወዝ ጭማሪ አድርገዋልምስል picture-alliance/ dpa

ቀድሞ በኢኮኖሚ እድገትዋ በአፍሪቃ ተጠቃሽ የነበረችዉ ዝንባቤ፣ ዛሪ ሊነገር በሚያዳግተዉ የገንዘብ ግሽፈት ዉስጥ በመዘፈቅዋ፣ ለምርጫዉ መሰናዶ ደጋፊዎችን ለመመስብ እንዲያስችል ገንዘብ ማሳተሟን ቀጥላለች። ታድያ ይህ አምባ ገነን መንግስት በገንዘብ ህትመት ለአመታት በመርዳት ላይ ያለዉ በጀርመን በሙንሽን ከተማ የሚገኘዉ ማተምያ ቤት መሆኑ ነገሩን አስገራሚ አድርጎታል። Giesecke & Devrient የተሰኘዉ የሙንሽኑ ማተምያ ቤት እና የዝንባቤ መንግስት ወዳጅነት የጀመሩት በ 70 ዎቹ አመታት በዝንባቤ የነበረዉ የ ስሚዝ መንግስት ከወደቀ ወድያ መሆኑ ታዉቆአል። የዶቸ-ቬለዉ ሉድገር ሻዶምስኪ ዝርዝር ዘገባዉን አጠናቅሮታል። አዜብ ታደሰ እንዲህ ታቀርበዋለች።