1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማሕበራዊ ዕድገት ሁኔታ በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ መጋቢት 11 2005

የተባበሩት መንግሥታት የልማት ዕቅድ ተቋም UNDP ባለፈው ሣምንት መጨረሻ ላይ Human Development Index በመባል የሚታወቅ የያዝነውን የጎርጎሮሳውያኑን 2013 ዓ-ም የማሕበራዊ ልማት ዝርዝር ማውጣቱ አይዘነጋም።

https://p.dw.com/p/180Hv
TO GO WITH STORY BY JENNY VAUGHAN This photo taken on May 22, 2012, shows a view of the controversial Gibe III dam under construction in Ethiopia’s Omo valley. The Gibe III dam is set to be completed by 2013 and will be Africa’s tallest at 243 metres high. The government says the Gibe III dam will boost development, give access to power for many Ethiopians -- about half of the population -- currently living without it, and generate revenue from the export of electricity to the region. But critics say Ethiopia must also consider the environmental and social impact it will have on some 500,000 people living downstream and at Lake Turkana in neighbouring Kenya, who rely on the river for their livelihood. AFP PHOTO / JENNY VAUGHAN (Photo credit should read JENNY VAUGHAN/AFP/GettyImages)
ምስል JENNY VAUGHAN/AFP/GettyImages

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በተከታታይ ከፍተኛ የኤኮኖሚ ዕድገት ማሳየቷ ቢነገርም በመረጃው ላይ ዘንድሮም በዝቅተኛው ቦታ ነው የሰፈረችው። የኤኮኖሚው ዕድገት ጭብጥ በሆነ ማሕበራዊ ዕርምጃ በሚገባ አልተንጸባረቀም ማለት ነው። ዘገባው ኢትዮጵያ ከ 187 ሃገራት መካከል በ 173ኛው ቦታ ላይ እንደምትገኝ ያመለክታል።

እርግጥ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የሚሌኒየም ዕቅድ ገቢር መሆን ከጀመረበት ከ 2000 ዓ-ም ወዲህ ቢቀር በሶሥት ግቦች በጤና ጥበቃ፣ በትምሕርትና የሕጻናትን ሞት መጠን በመቀነስ ረገድ ጠቃሚ ዕርምጃ እንዳደረገች በምዕራቡ ዓለም ጭምር በየጊዜው ሲነገር ነው የቆየው።

knowledge, experience and resources to help people build a better life. United Nations Development Program logo, graphic element on white
ምስል APGraphics

ይሁንና ዓመታዊው ዘገባ እንዳመለከተው አገሪቱ በማሕበራዊው ልማት ዝርዝር ላይ አሁንም በዝቅተኛው ቦታ መገኘቷ፤ በሌላ አነጋገር አገሪቱ አሁንም የድሃ ድሃ ከሚባሉት የመጨረሻ ሃያ ሃገራት ተርታ እንዳለች መቀጠሏ ብዙ ጥያቄዎችን የሚያስነሣ ነው። ኢትዮጵያ ለነገሩ ባለፉት ዓመታት ከምዕራቡ ዓለም በቢሊዮን የሚቆጠር ከፍተኛ የገንዘብ ዕርዳታ ከሚያገኙት ቀደምት ሃገራት አንዷ ሆና ቆይታለች።ይህም ሆኖ ግን ከሶሥት ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ ዛሬም በውጭ የምግብ ዕርዳታ ላይ ጥገኛ ሲሆን የሚሌኒየሙ ግቦች ቀደም ሲል ከተጠቀሱት ባሻገር በተለይም ድህነትን በግማሽ በመቀነሱ ረገድ የጊዜ ገደቡን ጠብቆ ቢቀር የተቃረበ ውጤት እንኳ ማሣየቱ የሚያጠያይቅ ነው።

በነገራችን ላይ የማሕበራዊው ልማት ዘገባ በታዳጊው ዓለም በአጠቃላይ መሻሻል መታየቱን ሲያረጋግጥ ችግሩ እንዳለ ከቀጠለባቸው 25 ሃገራት 24ቱ አፍሪቃ ውስጥ እንደሚገኙም አመልክቷል። ለማሕበራዊው ልማት መሻሻል ሁል-አቀፍ የሆነ ሰፊ ሕብረተሰባዊ ዕርምጃ አስፈላጊ ሲሆን የኤኮኖሚ ዕድገትን ወደ ማሕበራዊ ዕርምጃ መለወጥና የኤኮኖሚ ብቃትን ማዳበር መቻሉም አንዱና ዋነኛው ቅድመ-ግዴታ ነው።World Economic Forum የተሰኘው የዓለም ኤኮኖሚ መድረክ ባለፈው ሣምንት ማብቂያ የ 2012/13 ዓለምአቀፍ የኤኮኖሚ ብቃት፤ የምርታማነት ዘገባውን ሲያቀርብ ኢትዮጵያ እዚህም ከ 143 ሃገራት 121ኛ ሆና ነው የተቀመጠችው። በአፍሪቃ ውስጥ ደግሞ ከ 37 ሃገራት መካከል 22ኛውን ቦታ ይዛለች።

Mar 14, 2013 - Mexico City, Mexico - Administrator of the United Nations Program for Development (UNDP) HELEN CLARK and President of Mexico ENRIQUE PENA NIETO during 2013 Human Development Report 'The Rise of the South: Human Progress in a Diverse World
የ2013 ዘገባምስል picture alliance/ZUMAPRESS.com

ለግንዛቤ ያህል ዘገባው ደቡብ አፍሪቃን፣ ሞሪሺየስንና ሩዋንዳን በአፍሪቃ ቀደምት ሲያደርግ የመጨረሻውን ቦታ የያዙት ቻድ፣ ጊኒና ሢያራ ሌዎን ናቸው። እንግዲህ የኤኮኖሚ ብቃት ወይም አቅም ግምቢያውም ብዙ መሻሻልን የሚጠይቅ መሆኑ አልቀረም። ይህ በተለይ በዝግጅታችን ሁለተኛ ክፍል በሰፊው የምናተኩርበት ጉዳይ ይሆናል። ለዛሬው የኢትዮጵያን ማሕበራዊ ልማትና የኤኮኖሚ ይዞታ በተመለከተ በዚህ በጀርመን የአፍሪቃ የሰላምና የምጣኔ-ሃብት ዕድገት አማካሪ የሆኑትን የኤኮኖሚ ምሁር ዶር/ፈቃደ በቀለን አነጋግሪያለሁ፤ ያድምጡ!

መሥፍን መኮንን

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ