1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማሽን መስፋፋት የሚያስከትለዉ ችግር

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 25 2009

ጉዳቱ በአብዛኛዉ የሚደርሰዉ ደግሞ በአዳጊ ሐገራት ዜጎች ላይ ነዉ።ፕሬዝደንቱ ኢትዮጵያን በሥም ጠቅሰዉ በግንባር ቀደምትነት ለችግር ከሚጋለጡ ሐገራት አንዷ ናት ብለዋታል

https://p.dw.com/p/2cHsN
Jim Yong Kim
ምስል picture alliance/AP Images/AP Photo/C. Kaster

(Beri.WDC) Weltbank-Äthiopien - MP3-Stereo

በሰዉ ኃይል የሚከናወኑ ሥራዎች ማሽን እየተካቸዉ በመጣ ቁጥር የአዳጊ ሐገራት ዜጎች ለሥራ አጥነት እንደሚዳረጉ የዓለም ባንክ አስታወቀ።የዓለም ባንክ ፕሬዝደንት ኪም ዮንግ ጂም ባለፈዉ ሰኞ እንዳስታወቁት የማሽኖች አገልግሎት መሥፋፋት የጥቅሙን ያክል የሚያስከትለዉ የሥራ አጥ ቁጥርም ከፍተኛ ነዉ።ጉዳቱ በአብዛኛዉ የሚደርሰዉ ደግሞ በአዳጊ ሐገራት ዜጎች ላይ ነዉ።ፕሬዝደንቱ ኢትዮጵያን በሥም ጠቅሰዉ በግንባር ቀደምትነት ለችግር ከሚጋለጡ ሐገራት አንዷ ናት ብለዋታል።የዋሽግተን ዲ ሲዉ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ