1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

ዓርብ፣ ጥቅምት 5 2014

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጸም ጦርነት፤ የንጹሐን ዜጎች ሞት፣ መፈናቀል እንዲሁም የንብረት ውድመት የየዕለት ዜና ከሆነ ሰነባብቷል። ወቅታዊ ጉዳዮችን የሚያስተናግዱት ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችም በአንድ በኩል መረጃዎችን ማጋራታቸው እንዳለ ሆኖ ሌላ የጦር አውድማ ሆነዋል።

https://p.dw.com/p/41kYi
Symbolbild Hass Im Netz
ምስል picture-alliance/APA/picturedesk/H. Fohringer

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጸም ጦርነት፤ የንጹሐን ዜጎች ሞት፣ መፈናቀል እንዲሁም የንብረት ውድመት የየዕለት ዜና ከሆነ ሰነባብቷል። ወቅታዊ ጉዳዮችን የሚያስተናግዱት ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችም በአንድ በኩል መረጃዎችን ማጋራታቸው እንዳለ ሆኖ ሌላ የጦር አውድማ ሆነዋል። እንደዜጋ የሁሉን ስሜት የሚቆነጥጡ ጉዳዮች ላይ የሚሰነዘሩት አስተያየቶች ዛሬ ዛሬ እንኳን በመደበኛው መገናኛ ብዙሃን መድረክ ዳግም ሊደመጡ ቀርቶ ባሉበትም እስከፍጻሜያቸው ለማንበብ ሰብዕናን ይፈታተን ይዟል። ከትግራይ ክልል አልፎ ወደ ጎረቤት አፋር እና አማራ ክልል የተስፋፋው በከባድ መሣሪያዎች የታጀበው ጦርነት የሚያረግፈው የሰው ሕይወት የሚያወድመው ንብረት ማሳሰቡ ቢቀር፤ በለው በለው በሚሉ እና በወገን ስቃይ በሚያላግጡ አስተያየቶች ባይሰጡበት ሰው ያሰኛል። እያሰለሰ ንጹሐን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የሚስተናገድበት ምዕራብ ኢትዮጵያም እንዲሁ የማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ተጠቃሚዎች ጎራ ለይተው የሚሰዳደቡበት ሆኗል። በዚህ መሀል ግን ለመገደላቸው ምክንያቱን የሚያውቁ ንጹሐን ባላሰቡበት ወቅትና ቦታ ሕይወታቸው መቀጠፉ ቀጥሏል። ባለፉት ቀናት በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ ተጠቃሚዎች ዘንድ በአንድ አቅጣጫ ያተኮረ አስተያየት ያስተናገደው የተመድ የድርጅቱን መረጃዎች አሹልከዋል በሚል ኢትዮጵያ ውስጥ ይሠሩ የነበሩ አንዲት አፍሪቃዊት ሴትን ከሥራቸው ማንሳቱን ያመለከተው ዜና ነው። በዚህም የተመድ እንዲሁም ዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎች ምዕራባውያን ሃገራት ኢትዮጵያ ላይ ጫና ማድረጋቸውን እንዲያቆሙ የሚለው ዘመቻ መሰል እንቅስቃሴ ብዙዎች በጋራ መንፈስ የተሳተፉበት ሆኖ ታይቷል። እኛም በሰሜን ኢትዮጵያ የተጠናከረውን ውጊያ፣ በወለጋ የተፈጸመውን የንጹሐን ግድያ እና ከኢትዮጵያ የተጠሩትን የተመድ ሠራተኛ አስመልክቶ ከተሰጡ አስተያየቶች መድረካችንን የሚመጥኑ ያልናቸውን በመጠኑ እጠናቅረናል።

Symbolbild Twitter Konto
ምስል picture-alliance/dpa/A. Gombert

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ