1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማኦኮሞ የዱር እንሰሳት መጠለያ

ዓርብ፣ ግንቦት 30 2011

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የፓርክና የዱር እንስሳት ልማት ጥበቃ ሃላፊ አቶ ሳሙኤል አድማሱ ከማኦኮሞ የዱር እንሰሳት መጠለያ በቅርብ ርቀት ላይ በተቋቋመው የቶንጎ የስደተኞች ካምፕ ያሉ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ከመጠለያው በሚወስዱት የማገዶ እንጨት ምክንያት መጠለያው ጉዳት እየደረሰበት መሆኑን ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ፡

https://p.dw.com/p/3K2iv
Äthiopien Maokamo Waldgebiet
ምስል DW/N. Desalegn

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚገኙት አራት የዱር እንስሳት መጠለያ ስፍራዎች መካከል የማኦ-ኮሞ የዱር እንስሳት መጠለያ ስፍራ አንዱ ነው፡፡ ይህ የዱር እንስሳት መጠለያ ስፍራ በ2007 ዓ.ም ነበር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ባህልና ቱሪዝም  ከፌደራል የዱር እንስሳት ልማት  ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመሆን ጥናት በማካሄድ ስፋራው ዱር እስሳት መጠለያ እንዲሆን መወሰኑን  የክልሉ ባህል ቱሪዝም ያሳታወቀው፡፡

የዱር እንስሳት መጠለያ ስፍራው የክልሉን የአየር ሁኔታ ጠብቆ እንዲቆይና የበረሀማነትን መስፋፋትን ይገድባል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል ያሉት በቤ/ጉ/ክ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የፓርክና የዱር እንስሳትልማት ጥበቃ ዳይረክተር  ሆኑት አቶ ሳሙኤል አድማሱ በቅርብ ርቀት ላይ የተቋቋመው ቶንጎ ስደተኞች ካምፕ የሚኖሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በሚጠቀሙት የማገዶ እንጨት ምክንያት በስፍራው ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው ብለዋል፡፡

2304 ስኩር ኪ፣ሜ የሚሸፍነው የማኦ ኮሞ የዱር እንስሳት መጠለያ ስፍራ በርካታ እንስሳቶችንና ብርቅዬ አህዋፋትም ይገኙበታል፡፡ አካባቢው ለለስደተኞች ካምፕ ሲመረጥ በቂ ጥናት እንዳልተደረገ የተናገሩት አቶ ሳሙኤል ችግሩን ለመቅረፍም ከስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ጋር  እየሰሩ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

የስደተኞችን መጠለያ የማቋቋምና  በስደተኞች ላይ የሚደርሱትን ማናቸውንም እንቅስቃሴዎች በበላይነት የሚቆጣጠረው የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀን(ARRA) የተባለ ድርጅት .በበኩሉ ችግሩ መኖሩን አረጋግጠዋል፡፡ የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ያሲን አሊይ የተፈጥሮ ሀብቱ እንዳይባክን ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት አማራጭ ሀይል ኤጀንሲው እያቀረበ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ካምፖቹ ሲገነቡ በቂ ጥናት አልተደረጉም ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄም አቶ ያሲን ተከታዩን ምልሽ ሰጥተዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአራት በላይ የስደተኞች ካምፖች ያሉ ሲሆን 12317 ስደተኞች በቶንጎ የስደተኞች እንደሚገኙ ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የUNHCR  አሶሳ ቅርንጫፍን ዶቼቬለ በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ምላሽ ማግኘት አልቻለም፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ