የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተፈናቃዮች
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 30 2011ማስታወቂያ
ከአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን የተፈናቀሉ ሰዎች ወደቀያቸው እየተመለሱ መሆኑን የአማራ ክልል መንግስትና የየአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ክልሉ እንዳስታወቀው እስካሁን ወደ ቀያቸው የተመለሱት ቁጥር ከ13 ሺህ በላይ ነው። በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በአማራና በቅማንት ማህበረሰብ መካከል በዚህ ዓመት በተፈጠረው ግጭት ለተፈናቀሉት ሰዎች የመኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ መሆኑንም የክልሉ የምግብ ዋስትና መርሃ ግብር ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታውቋል። በግጭቱ በሁለቱም ዞኖች ህይወት ጠፍቷል፣ ከ6000 በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡ ዓለምነው መኮንን ከባሕር ዳር ዝርዝር ዘገባ አለው።
ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ