1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሌላ የመብራት ተስፋ

ዓርብ፣ ግንቦት 23 2011

የኢትዮጵያ ሕዝብ በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ዘንድሮም መብራቱ የኩራዝ ነዉ።ከኩራዝ ተላቅቋል ወይም የኤሌክትሪክ ኃይል ያገኛል የሚባለዉ የየከተማዉ ሕዝብም መብራት የሚያገኘዉ በቁነና ነዉ

https://p.dw.com/p/3JZl6
Äthiopien Gide III Staudamm
ምስል Getty Images/AFP

ሌላ የኤሌክትሪክ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ የሕዝብዋን የኃይል ፍጆታ የሚያረካ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ እንደሚገነባላት ቃል ሲገባ፣ ተስፋ ሲሰጥ፣ ቃል ተስፋዉ ሲበን ዓመታት ተቆጠሩ።የኢትዮጵያ ሕዝብ በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ዘንድሮም መብራቱ የኩራዝ ነዉ።ከኩራዝ ተላቅቋል ወይም የኤሌክትሪክ ኃይል ያገኛል የሚባለዉ የየከተማዉ ሕዝብም መብራት የሚያገኘዉ በቁነና ነዉ።ዛሬም ግን የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት «ኩራዛሕ በኤሌክትሪክ ኃይል ሊለወጥ ነዉ ይሉታል-ሕዝቡን።ባለስልጣናት እንደሚሉት ለ12 የገጠር ከተሞች መብራት የሚሰጡ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ግንባታ በቅርቡ ይጀመራል።

 ሰለሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ