1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የማይካድራ ጭፍጨፋ ተጠርጣሪዎች 

ሐሙስ፣ የካቲት 18 2013

አዲስ አበባ ያስቻለዉ ፍርድ ቤት የተጠርጣሪ ጠበቆች ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት ተጠርጣሪዎች አደረሱት የተባለዉ ጥፋት በተናጥል እንዲቀርብ፣ የተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብት ይዞታ እንዲሻሻልም አዟል።

https://p.dw.com/p/3pvR0
Äthiopien | Tigray | Massaker in Mai Kadra
ምስል Eduardo Soteras/AFP/Getty Images

የማይካድራ ጭፍጨፋ ተጠርጣሪዎች ምርመራ

ማይካድራ-ትግራይ ዉስጥ ባለፈዉ ጥቅምት በሠላማዊ ነዋሪዎች ላይ በተፈፀመዉ ጭፈጨፋ የተጠረጠሩ ሰዎችን ጉዳይ የሚመረምረዉ ፖሊስ  ምርመራዉን በ11 ቀናት ዉስጥ እንዲያጠናቅቅ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዘዘ።ዛሬ አዲስ አበባ ያስቻለዉ ፍርድ ቤት የተጠርጣሪ ጠበቆች ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት ተጠርጣሪዎች አደረሱት የተባለዉ ጥፋት በተናጥል እንዲቀርብ፣ የተጠርጣሪዎች ሰብአዊ መብት ይዞታ እንዲሻሻልም አዟል።ከ600 በላይ ሠላማዊ ሰዎች በተገደሉበት በማይካድራዉ ጭፍጨፋ ከሚጠረጠሩት ዛሬ ጉዳያቸዉ የታየዉ የ36ቱ ነዉ።

 ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለስ