1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሜርክል ኦባማ ዉይይትና የጀርመን አሜሪካ ግንኙነት

ሰኞ፣ ሰኔ 22 2001

መራሔተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል በብዙ መንገድ የመጀመሪያ ናቸዉ።የአደናወርን መርሕ ይቀበሉ፥ የሽሩደርን ሕልም ይጋሩ ይሆናል።ለዚሕ ያበቋቸዉን ሔልሙትን ኮልን ማድነቃቸዉ አይቀርም።በብዙ ነገር በተለይ ደግሞ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ባለዉ ግንኙነት ግን ሜርክል እሳቸዉን ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/IdZJ
ምስል AP

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ ሥልጣን ከያዙ ወዲሕ ካንዴም-ሁለቴ ጀርመንን ጎብኝተዋል።ከጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥት ከአንጌላ ሜርክል ጋር ቢያንስ አራቴ ተወያይተዋል። የኦባማ የመጨረሻ ጉብኝት-ዉይይት ወር ሳይደፍን የጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት ዋሽግተን ደርሰዉ ተመለሱ።ቅዳሜ።ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።የሁለቱ መሪዎች የድግግሞሽ ጉብኝት-ዉይይት ምክንያት መነሻች፤ የአለም አንደኛና ሰወስተኛ ሐብታም ሐገራት የወዳጅነት ዳራ ማጣቀሻ፤ እንድምታዉ መድረሻችን ነዉ ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።

dw,

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ