1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የሜርክል የዋሽግተኝ ጉብኝ

ዓርብ፣ መጋቢት 8 2009

ፕሬዝደንት ትራምፕ ከምረጡኝ ዘመቻቸዉ ጊዜ ጀምረዉ ጀርመንና የአዉሮጳ ሕብረትን በማናናቃቸዉ ሰበብ በሁለቱ ሐገራት መካከል የተፈጠረዉን አለመግባባት ለማስወገድ ይረዳል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል

https://p.dw.com/p/2ZQaW
USA Merkel und Trump
ምስል Reuters/J. Bourg

(Beri.WDC) Merkel USA Besuch - MP3-Stereo

ዩናይትድ ስቴትስን የሚጎበኙት የጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት ወይዘሮ አንጌላ ሜርክል ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ከአሜሪካዉ ፕሬዝደን ዶናልድ ትራም ጋር ይነጋገራሉ።ዉይይቱ፤ ፕሬዝደንት ትራምፕ ከምረጡኝ ዘመቻቸዉ ጊዜ ጀምረዉ ጀርመንና የአዉሮጳ ሕብረትን በማናናቃቸዉ ሰበብ በሁለቱ ሐገራት መካከል የተፈጠረዉን አለመግባባት ለማስወገድ ይረዳል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል።ዩናይትድ ስቴትስን ባለበሰዉ የበረዶ ክምር ምክንያት ጉዟቸዉ ካለፈዉ ማክሰኞ ትናንት የተዛወረዉ ሜርክል ወደ ዋሽግተን የተጓዙት የጀርመን ትላልቅ ኩባንያ ባለቤቶችና ሐላፊዎችን አስከትለዉ ነዉ።ትራምፕና ሜሪክል ዉይይታቸዉ እንዳበቃ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ።የዋሽግተኑ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ