1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሜርክል መልካም ምኞት

ሐሙስ፣ መጋቢት 27 2010

ሜርክል ለአዲሱ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት ሀገሪቱ የተጋረጡባትን ከባድ ፈተናዎችን ማለፉ እንዲሳካላቸው ተመኝተዋል።

https://p.dw.com/p/2vZ4w
Äthiopien Vereidigung Premierminister Abiy Ahmed
ምስል picture-alliance/AA/M. W. Hailu

አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያን ቀውስ ይወጣሉ ከሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ጋር ፖለቲካዊ ውይይት ያካሂዳሉ ብለው  ተስፋ እንደሚያደርጉ የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል  አስታወቁ ። ሜርክል ለዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት ሀገሪቱ የተጋረጡባትን ከባድ ፈተናዎችን ማለፉ እንዲሳካላቸው ተመኝተዋል። ለረዥም ጊዜ የዘለቀው የሁለቱ ሀገራት የቅርብ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፍላጎታቸው መሆኑን ያሳወቁት ሜርክል በደስታ መግለጫቸው መንግሥታቸው ለብልጽግና እና ለተጨማሪ ነጻነት ጉዞ ላይ የምትገኘውን ኢትዮጵያን ይደግፋል ብለዋል።

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ