1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሜርክል ጉብኝት በእስራኤል

ማክሰኞ፣ የካቲት 18 2006

የኢራን የኑክሌር መርሐ-ግብር፥ የእስራኤልና የፍልስጤሞች ድርድር እንዲሁም እስራኤል በሐይል በያዘችዉ የፍልስጤም ግዛት የምታስገነባዉ የአይሁድ የሠፈራ መንደር ሁለቱ ወገኖች ከተነጋገሩባቸዉ ጉዳዮች ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ

https://p.dw.com/p/1BFDs
ምስል picture-alliance/dpa

የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል በእስራኤል የሚደርጉትን ጉብኝት ዛሬም ቀጥለዉ ዉለዋል።ሜርክል ከፍተኛ የካቢኔ ባለሥልጣኖቻቸዉን አስከትለዉ ትናንት ወደ እስራኤል የተጓዙት ሁለቱ ሐገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት የጀመሩበትን ሐምሳኛ ዓመት ለማክበር ነዉ።ሜርክል የመሩት የጀርመን የባለ ሥልጣናት ቡድን ከእራኤል አቻዎቹ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል።የጋራ ስምምነትም ተፈራርሟል።የኢራን የኑክሌር መርሐ-ግብር፥ የእስራኤልና የፍልስጤሞች ድርድር እንዲሁም እስራኤል በሐይል በያዘችዉ የፍልስጤም ግዛት የምታስገነባዉ የአይሁድ የሠፈራ መንደር ሁለቱ ወገኖች ከተነጋገሩባቸዉ ጉዳዮች ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።የጉብኝትና የዉይይቱን ሒደት በተመለከተ የሐይፋ-ወኪላችን ግርማዉ አሻግሬን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ግርማዉ አሻግሬ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ