1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምህረት አዋጁ መገባደድ እና የኢትዮጵያዉያን ሁኔታ

ዓርብ፣ ሐምሌ 14 2009

የሳዉድ አረቢያ መንግሥት በሀገሪቱ የሚገኙ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸዉ የዉጭ ዜጎች ግዛቱን ለቀዉ እንዲወጡ መጀመሪያ የሰጠዉ የዘጠና ቀናት የምረት ጊዜ አብቅቶ፤ ተጨማሪ ያራዘመዉም የ30 ቀናት የምህረት ቀነገደብ ሊያበቃ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተዉታል።

https://p.dw.com/p/2gz2Z
Rückkehrer Äthiopien Saudi Arabien Riad
ምስል DW/S.Sibiru

Q&A Saudi Amnesty and Ethiopian - MP3-Stereo

እስካሁንም ግን ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸዉ ሳዉዲ ዉስጥ እንደሚኖሩ የሚገመተዉ ከመቶ ሺህ የሚበልጡ ኢትዮጵያዉያን ተጠቃለዉ ወደ ሀገር እንልገቡ ነዉ የሚነገረዉ። የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ ሀገር የተመለሱት ቁጥር 60 ሺህ እንደሚደርስ ይገልጻል። የመጓጓዣ ሰነድ ማለትም ሊሴ ፓሴ የወሰዱት ከ120 ሺህ እንደሚበልጡ ነዉ የተሰማዉ። ከሰሞኑ ያን ያህል እንቅስቃሴ እንደሌለ የጠቆመን ጅዳ የሚገኘዉ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የአዉሮፕላን ትኬት ዋጋ መናር ብዙዎቹን ተስፋ እንዳስቆረጠ ገልጾልናል። ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ ነብዩን አነጋግሬዋለሁ።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ