1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምላጂች መያዝ ና የስርብያ የወደፊት ዕጣ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 23 2003

ሰርብያ የሄጉ ዓለም ዓቀፍ ፍርድ ቤት በጦር ወንጀለኝነት የሚፈልጋቸውን የቦስኒያ ሰርብ ጦር አዛዥ ጀነራል ራትኮ ምላዲችን ወደ ሄግ ላከች ።

https://p.dw.com/p/RR3j
ምስል dapd

ምላዲች ከተከሰሱባቸው ውስጥ 11 የጦርና ሁለት የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ይገኙበታል ። ከዛሬ 16 ዓመታት ወዲህ ፣ የስሬብሬኒስካ ከተማ እና የርሳቸው ስም ተነጣጥለው አያውቁም ። የጀነራል ራትኮ ምላጂች ስም ሲነሳ ስሬብሪኒስካም አትቀርም ።

ምላጂች በዚህች ከተማ .. 1995 በቦስኒያ ሙስሊሞች ላይ የተካሄደውን አስከፊ ጭፍጨፋ ጨምሮ ሌሌች የጦር ወንጀሎችን በማቀድና በማስፈፀም ዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ በጦር ወንጀለኝነት ሲያድናቸው የቆየ ጀነራል ናቸው በስሬብሬኒስካ በርሳቸው የጦር አዛዥነት የሰርብ ጦር 8 ሺህ በላይ ሙስሊም ወንዶችን በመጨፍጨፍ ይወነጀላሉ ከዚህ በተጨማሪም በክሮኤሽያ በተፈፀሙ የጦር ወንጀሎችና የቦስኒያን መዲና ሳራዮቮን 3 ዓመት ተኩል በላይ ከበው በማስጨነቅም የሄጉ ፍርድ ቤት ተጠያቂ ያደርጋቸዋል በነዚህ ተደራራቢ ወንጀሎች የሚፈለጉት ጀነራል ራትኮ ምላጂች የመያዛቸው ዜና ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ይፋ እንደሆነ ልዩ ልዩ አስተያየቶችን አስከትሏል የምላዲች መያዝ ለአውሮፓ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ እና ቤልግሬድም በአውሮፓ ህብረት እንድትታቀፍ ማድረግ የሚያስችል አንድ ትልቅ እርምጃ ተብሎ ሲወሰድ በሀገር ውስጥ ደግሞ ተቃውሞ ቀስቅሷል የቀድሞ የሰርብ ጦር አዛዥ ራትኮ ምላዲች መያዝ ያስከተላቸው እነዚህ ሁለት የሚቃረኑ ሁነቶች እንዴት ይታያሉ ? በወደፊቱ የሰርቢያ የፖለቲካ አካሄድ ላይስ ምን ዓይነት ተፅዕኖ ያሳድሩ ይሆን ? ለፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ ያነሳኋቸው ጥያቄዎች ናቸው

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ