1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምሕረት ቅዱስ ዓመት ክብረ በዓል በቫቲካን

ማክሰኞ፣ ኅዳር 28 2008

የሮማዉ ካቶሊካዊት ቤተ- ክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን እና ፖለቲከኞች በተገኙበት በቫቲካን ታላቅ ሀይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት የምሕረት ቅዱስ ዓመት ክብረ በዓልን በይፍ ከፈቱ።

https://p.dw.com/p/1HJM9
Vatikan Heiliges Jahr Papst Franziskus öffnet die Heilige Pforte
ምስል Reuters/A. Bianchi

[No title]

በከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ በተካሄደው በዚህ ታላቅ ክብረ በዓል ላይ ስርዓተ-ፀሎት ያደረጉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ «ፍርኃትና ሰቆቃን ወደኃላ መጣል ያስፈልገናል» ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። በኢጣልያ ዋና ከተማ በሮም የፀጥታ ጥበቃው ተጠናክሮ በአብዛኛዉ ቦታ የበረራ እገዳ ተደርጎ ነበር ፤ ማንኛዉም አይነት ነዳጅም ሆነ የጦር መሣርያን እና ተቀጣጣይ ነገሮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎe ወደ ከተማይቱ ማዕከል እንዳይወጡ ተክልክለውም ነበር ። እዚህ ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በሮማ ኢጣልያ ወኪላችንን ተክለዝጊ ገብረየሱስን፤ ስለ ምኅረት ቀን ምንነትና ዝግጅቱ ጠይቄዉ ነበር

ተክለዝጊ ገብረየሱስ

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ