1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምሥራቅ አፍሪቃ ረሐብ እና የተመድ የርዳታ ጥሪ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 19 2003

ለረሐብ ለተጋለጠዉ የምሥራቅ አፍሪቃ ሕዝብ ለሚቀጥሉት አምስት ወራት ምግብና መድሐኒት ለማቅረብ ከአንድ መቶ አስራ-አንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ እርዳታ እንደሚያስፈልገዉ የአለም ምግብ ድርጅት አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/RcIF
ምስል dapd

በኢትዮጵያ የድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ ዩዲት ሹለር እንደሚሉት ዓለም ብዙ ቢረዳም ተረጂዉ ከከፋ ችግር ለማዳን ተጨማሪ ዕርዳታ መጠየቅ ግድ ነዉ። የዓለም የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነር የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ ክሱት ገብረ-እግዚአብሔር በበኩላቸዉ መስሪያ ቤታቸዉ ረሐብ ያሰደዳቸዉን የሶማሊያ ዜጎች እየረዳ መሆኑን አስታዉቀዋል።ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ሁለቱን ባለሥልጣናት አነጋግሯል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ነጋሽ መሀመድ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ