1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምሥራቅ አፍሪቃ ታዋቂ አትሌቶች አሰልጣኝ ተጠርጥሮ መታሰር

ማክሰኞ፣ ሰኔ 14 2008

የአትሌቶች አሰልጣኝ ጃማ ኤደን በስጳኝ የባርሰሎና ከተማ አቅራቢያ ባረፉበት ሆቴል ትናንት በቁጥጥር ስር ዋሉ። ሶማልያዊው አሰልጣኝ የታሰሩት የስጳኝ ፖሊስ በክፍላቸው ድንገተኛ ፍተሻ ካደረገ እና የተከለከሉ የደም ሴሎችን የሚጨምር ንጥረ ነገር፣ እንዲሁም ፣ ወደ 60 የሚጠጉ መርፌዎች ካገኘባቸው በኋላ ነው።

https://p.dw.com/p/1JAmw
Symbolbild Doping
ምስል picture-alliance/dpa/G. Breloer

[No title]

በወቅቱ ስድስት የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር ሀኪሞች እና የስጳኝ ፀረ ጉልበት ሰጪ ንጥረነገር ተቋም በጋራ ለስልጠና ከአሰልጣኝ ጃማ ኤደን ጋር የተገኙትን ከ25 የሚበልጡ አትሌቶችን የደም ናሙና ለምርመራ ወስደዋል።

ሃይማኖት ጥሩነህ

አዜብ ታደሰ