1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምርጫ ቦርድ ማስጠንቀቂያ

ዓርብ፣ ጥር 1 2007

አንድነት የተጠየቀውን አሟልቶ ማሳወቁን ሆኖም መልስ ሳያገኝ በመገናኛ ብዙሃን ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ይናገራል። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አንድነት ለዲሞክራሲና ፍትኅ ፓርቲ (አንድነት) እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በውሳጣቸው ያለውን አለመግባባት በሕጋዊ መንገድ ካልፈቱ ርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠንቅቋል።

https://p.dw.com/p/1EI9R
Büro des National Electoral Board of Ethiopia NEBE
ምስል DW

ርምጃው ምን እንደሚሆን ግን በግልፅ አላሳወቀም። አንድነት በበኩሉ የተጠየቀውን አሟልቶ ማሳወቁን ሆኖም መልስ ሳያገኝ በመገናኛ ብዙሃን ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ይናገራል። የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት አንድነት በምርጫው እንዳይሳተፍ ገዥው ፓርቲ ተፅእኖ እያደረገበት መሆኑን ተናግረዋል ። ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር ልኮልናል።

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ