1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምርጫ ዋዜማ ዉጥረት በዴሞክራቲክ ኮንጎ

ሐሙስ፣ መስከረም 18 2004

በመጪዉ ጥቅምት ወር አጋማሽ ገደማ አጠቃላይ ምርጫ ለማካሄድ የተዘጋጀችዉ ማዕከላዊ አፍሪቃዊቷ አገር ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ከወዲሁ የፖለቲካ ዉጥረት እንደሰፈነባት እየተነገረ ነዉ።

https://p.dw.com/p/RoRB
ፕሬዝደንት ጆሴፍ ካቢላምስል AP Photo

የተፎካካሪ ፓርቲዎች ብዛት አራት መቶ መድረሱ በራሱ ህዝቡን ግራ ሊያጋባና የምርጫ ድምፁንም ሊያሳሳዉ እንደሚችል የፖለቲካ ታዛቢዎች እናገራሉ። ፓርቲዎቹ ችግር የሚሉት ግን ነፃ ምርጫ አይኖርም የሚለን ነዉ። በኮንጎ ሰላማዊ ምርጫ ለማካሄድ እንዲቻል አዲስ አበባ ላይ የአፍሪቃዉ ኅብረት ተቀናቃኝ የኮንጎ ፖለቲካ ፓርቲዎችን በማነጋገር ስምምነት አፈራርሟል። ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በግጭት ጦርነት የምትታመሠዉ አገር ምርጫዉን በስኬት ካላጠናቀቀች ጦሱ ማዕከላዊ አፍሪቃን ሊያናጋ የሚችል ፖለቲካዊ ቀውስ እንዳታስከትል እንደሚሰጋም ኅብረቱ አስጠንቅቋል።

ታደሰ እንግዳዉ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ