1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ያቀረበው ስሞታ

ሰኞ፣ የካቲት 2 2012

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በሐረሪ ክልል ፖሊስ ላይ ያቀረበው ስሞታ በቅርቡ በሀረር ከተማ ከጥምቀት በዓል ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ኹከትና ብጥብጥ ተከትሎ የክልሉ መንግሥት እና በተለይም የፀጥታ ኃይሉ ድርጊት አግባብ አይደለም ሲል የምሥራቅ ሀርጌ ሀገረ ስብከት ተቃወመ።

https://p.dw.com/p/3XZIV
Äthiopien | Äthiopische Orthodoxe Kirche
ምስል DW/M. Teklu

ሀገረ ስብከቱ በሐረሪ ክልል ፖሊስ ላይ ያቀረበው ስሞታ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በሐረሪ ክልል ፖሊስ ላይ ያቀረበው ስሞታ በቅርቡ በሀረር ከተማ ከጥምቀት በዓል ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ኹከትና ብጥብጥ ተከትሎ የክልሉ መንግሥት እና በተለይም የፀጥታ ኃይሉ ድርጊት አግባብ አይደለም ሲል የምሥራቅ ሀርጌ ሀገረ ስብከት ተቃወመ። ሀገረ ስብከቱ ባወጣው መግለጫ የፀጥታ ኃይሉ ከበዓሉ ጋር በተያያዘ በተከሰተው ኹከትና ግርግር ሊጠየቁ ይገባቸው የነበሩ አካላት ላይ ሳይሆን በዓሉን ለማክበር በወጣው ሕዝብ ላይ መሣርያ ተኩሷል ፤ አስለቃሽ ጭስ ተጠቅሟል ፤ ንብረት እንዲወድም ዕድል ሰጥቷል ብሏል። የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮምሽን በበኩሉ ፖሊስ ምንም ዓይነት አስለቃሽ ጭስ እና ኃይል እንዳልተጠቀመ በመግለፅ፤ በየትኛውም አግባብ የሚቀርቡ ቅሬታዎች ካሉ በጋራ ተቀራርቦ ለማየት ዝግጁ መሆኑንን አመልክቷል።

Äthiopien | Äthiopische Orthodoxe Kirche
ምስል DW/M. Teklu


መሳይ ተክሉ

ታምራት ዲንሳ

ሸዋዬ ለገሠ