1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምክርቤት ምርጫ በጀርመን

ሐሙስ፣ ጥር 14 2001

የጎርጎሮሳውያኑ 2009 ዓመተ ምህረት በጀርመን በርከት ያሉ ዐበይት ምርጫዎች የሚካሄዱበት ዓመት ነው ።

https://p.dw.com/p/GeQQ
ሮላንድ ኮኽምስል AP

በ2009 የአንዳንድ ፌደራል ክፍላተ ሀገራት ፣ እንዲሁም አጠቃላይ ምርጫ የሚካሄድ ሲሆን ፤ በዚሁ ዓመት ህዝቡ ለአውሮፓ ፓርላማ ዕንደራሴዎችም ድምፅ ይሰጣል ። በፌደራዊ ክፍለ ሀገር ደረጃ ለ2009 ከታቀዱት ምርጫዎች አንዱ ዋነኛውን የጀርመን የንግድ ማዕከል ፍራንክፈርትን በሚያጠቃልለው በሄሰን ፌደራዊ ክፍለ ሀገር ባለፈው ዕሁድ የተካሄደው ምክርቤታዊ ምርጫ ነው ።