1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምዕራብ ሸዋ ተፈናቃዮች የደረሰባቸዉ ችግር

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 19 2007

በኦሮምያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረደ በተነሳዉ ግጭት 85 አባዎራዎች ማለትም 305 ሕዝብ በአጎራባች ደቡብ ክልል መፈናቀሉንና 124 ቤቶች መቃጠላቸዉን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮኃንስ ገ/ እግዚአብሄር የላከልን ዘገባ ያመለክታል።

https://p.dw.com/p/1GLRr
Karte Äthiopien englisch


ተፈናቃዮቹ በአጎራባች ቀበሌ በተፈጠረ ግጭት አንድ ሰዉ መሞቱንና ይህን ተከትሎ ቤት ንብረታቸዉ ተቃጥሎ እስካሁን ስደት ላይ እንደሚገኙ መናገራቸዉ ተመልክቶአል። የወረዳዉ ፀጥታ ዘርፍ በበኩሉ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ቤት ንብረት ያቃጠሉትን ለሕግ ማቅረቡንና ተፈናቃዮችን ለማቋቋም ከሕዝብ ጋር በመሆን እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልፆአል።

ዮኃንስ ገ/ እግዚአብሄር


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ