1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች ሲገመገሙ

እሑድ፣ መስከረም 23 2008

የተመድ ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት በመላዉ ዓለም ለማሳካት ያቀዳቸዉ የምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች ለተግባራዊነታቸዉ የታቀደዉ ጊዜ ከሶስት ወራት በኋላ ያበቃል።

https://p.dw.com/p/1Ghwr
Müttergesundheit MDG-Plakat in Ghana
ምስል M.Hoegen

የምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች ሲገመገሙ

የመንግሥታቱ ድርጅት በየሀገሩ ያካሄደዉን ቅኝት መሠረት አድርጎም የልማት እቅዶቹ ሙሉ ለሙሉ አለመሳካታቸዉን ከአንድ ዓመት በፊት ይፋ አድርጓል። በአንዳንድ ሃገራት የሚታየዉን አስከፊ ድህነት እና ረሃብ ፈፅሞ ለማጥፋት ባይቻልም በዚህ ጊዜ መቀነስ መቻሉ፤ መዳን ሲቻል ህይወት ቀጣፊ የሆኑ በሽታዎች የሚያደርሱት ጉዳት ዝቅ ማለቱ፤ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት እና የጤና አገልግሎት ሽፋን ከ15ዓመታት በፊት ከነበረዉ ጨምሮ መታየቱ አዎንታዊ ዉጤት መሆኑ ተመዝግቧል። በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በኒዉዮርክ የተከፈተዉ የተመድ 70ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ስምንቱን የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦች በ17 ዘላቂ የልማት ግቦች ተክቷል። ተግባራዊነታቸዉም በመጪዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት መባቻ ይጀመራል። ኢትዮጵያ ከልማት ግቦቹ የተወሰኑትን ማሳካቷ ተገለጿል። ዶቼ ቬለ ለዚህ ሳምንት የአምዓቱን የልማት ግቦች እና ስኬት በመቃኘት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለተተለሙ የልማት ግቦች አተገባበር ይሞክራል።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ