1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምድር ነውጥ በኢጣልያ፣

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 1 2001

ዓለማችን፣ በዚህ ክፍለ-ጊዜ ፣ አልፎ-አልፎ እንደጠቀስነው፣ የላይኛው አካልዋ፣ የብሱም ሆነ ባህሩ ይብረድ እንጂ ውስጠኛው ክፍሏ ኃይለኛ ሙቀት ያለው ሲሆን፣

https://p.dw.com/p/HU0l
የምድር ነውጥ ያንቀጠቀጠው የኢጣልያ ክፍል፣ምስል AP

በተለያዩ ጊዜያት፣ በእሳተ ገሞራ አማካኝነት ይተነፍሳል።

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ እንኳ፣ በሰሜን አሜሪካ «ሪዳውት» የተሰኘው ፣ በአላስካ የሚገኘው እሳተ-ገሞራ ፈንድቶ ደመና መሰል ዐመድ 20 ኪሎሜትር ድረስ ወደ ሰማይ መትፋቱ የሚታውስ ነው።

ደቡብ አሜሪካ ውስጥ ፣ በደቡብ ምዕራብ ኮሎምቢያ የሚገኘው ጋሌራስ የተሰኘው እሰተ-ገሞራ፣ አምና በጥር ወር ከፈነዳ ወዲህ እንደገና ባለፈው የካቲት ተመሳሳይ ሁኔታ ታይቶበታል። በቺሌ ፣ በኤኳዶርም፣ እሳተ-ገሞራ በየጊዜው እየፈነዳ ፣ ህዝብ ማሸበሩ አልቀረም። በሩቅ ምሥራቅ፣ በጃፓንምከአንድ ወር ገደማ በፊት አሳማ በተባለው ተራራ የሚገኘው እሳተ-ገሞራ መፈንዳቱ አይዘነጋም።

በዓለም ውስጥ በዛ ያሉ እሳተገሞራዎች ያሏት ኢንዶኔሺያም ፣ ህዝቧ፣ በዚህ የተፈጥሮ ክስተት የቱን ያህል ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል ያውቃል። ኢትዮጵያ ውስጥ፣ የአሳተ-ገሞራ ምልክት ከሚታይባቸው 16 ያህል ቦታዎች አንዱ ፣ በአፋር የሚገኘው ኤርታሌ እሳተ-ገሞራ፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት አልፎ- አልፎ አሥፈሪነቱን ያሥመሰከረ ሲሆን በዚያው በአፋር ምድር፣ መሬቱን በመሰንጠቅ 6 ሜትር ገደማ ስፋት ያለው ጉድጓድ የፈጠረው እሳተ-ገሞራ፣ የታላቁን ስምጥ ሸለቆ የወደፊት ዕጣ-ፈንታ በተመለከተ ጠበብት ፣ ይኸው የአፍሪቃ ክፍል በውቅያኖስ ሊከፈል ይችላል በማለት መላ-ምት እንዲደረድሩ አብቅቷቸዋል።

በዓለም ውስጥ ፣ የአሳተ-ገሞራና የምድር ነውጥ አደጋ እጅግ ከሚያሠጋቸው አገሮች አንዷ ኢጣልያ ናት ። ማሥጋት ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ጊዜያት አደጋው ደርሶባታል። ከሰሞኑም፣ በመሃል ኢጣልያ የምትገኘው ተራራማ ከተማ፣ ላ ኪላ ፣ የዚሁ የምድር ነውጥ ሰለባ ሆናለች።

ተክሌ የኋላ፣

ነጋሽ መሐመድ፣