1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምግብ ርዳታ ለኢትዮጵያ

ሰኞ፣ ሰኔ 27 2003

ለኢትዮጵያ 38 ሚልዮን ዶላር የሚያወጣ የምግብ ርዳታ እንደምትሰጥ ቃል ገባች።

https://p.dw.com/p/RXaq
ምስል dpa

ብሪታንያ ብሪታንያ ይህን ርዳታ ባስቸኳይ ለማቅረብ የወሰነችው የተመድ የሰብዓዊ ርዳታ አስተባባሪ መስሪያ ቤት፡ ኦቻ በአፍሪቃ ቀንድ የሚገኙት ኢትዮጵያ፡ ሶማልያ፡ ጅቡቲ እና ዩጋንዳ ካለፉት ስድሳ ዓመታት ወዲህ ባካባቢው በተከሰተው አስከፊ ድርቅ ሰበብ በወቅቱ ብርቱ የምግብ እጥረት እንደሚያሰጋቸው ከጥቂት ቀናት በፊት ከገለጸ በኋላ ነው። በነዚሁ ሀገሮች ከአስር ሚልዮን የሚበልጥ ህዝብ አሳሳቢ የምግብ እጥረት አስግቶታል። የብሪታንያ የዓለም አቀፍ ልማት ሚንስትር አንድሩ ሚቼል እንዳስረዱት፡ በአሁኑ ጊዜ የሚታየው የምግብ ዋጋ ንረትም ችግሩን ሊያባብሰው እንደሚችል ነው ያሰጋው። በመሆኑም፣ ችግሩ እንዳይባባስ ብሪታንያ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት ለ 1,3 ሚልዮን ኢትዮጵያውያን የምግብ ርዳታ ታቀርባለች። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ላካባቢው ባስቸኳይ ርዳታ እንዲያቀርብ ሚቼል ተማጽነዋል። በድርቁ ሰበብ ከሶማልያ በየቀኑ ከአንድ ሺህ የሚበልጥ ሰው ኬንያ ወደሚገኘው የዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ እንደሚሄድ ግብረ ሰናዩ ድርጅት ኬር ኢንተርናሽናል አስታውቀዋል።

አርያም ተክሌ