1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምግብ እጥረት በኢትዮጵያ

Merga Yonas Bulaረቡዕ፣ ጥር 11 2008

ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚታየዉ ድርቅ እህል እና ቀንድ ከብቶች ላይ ባስከተለዉ ችግር በበልግ እና በመኸር ወቅት የሚሰበሰበዉ እህልም ሆነ የቀንድ ከብት ዉጤት በጣም እንደሚቀንስና ሃገሪቱ ዉስጥ ያለዉ የምግብ እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምር የረኃብ ቅድመ-ማስጠንቀቅያ ኔትዎርክ የሚባለዉ ድረ-ገፅ ያስነብባል።

https://p.dw.com/p/1Hh4H
Äthiopien Mädchen beim Wasserholen
ምስል picture alliance/Ton Koene

[No title]

በኢትዮጵያ ወደ 15 ሚሊዮን ሰዉ አሰቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያሰፈለገዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት «OCHA» ም አስታዉቀዋል። ከተጠቀሰዉ የምግብ ርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር Productive Saftey Net Program ማለት «የረኃብ ቅድመ-ማስጠንቀቅያ መረብ» ጠቃሚ የአደጋ መከላክያ መረብ መሰናዶ » ስር ገብተዉ እንደሚረዱና ቀሪዉ የአስቸኳ የምግብ ርዳታ ስር ሆኖ እንዲጠቀም ገፁ ይጋብዛል። ይሁን እንጅ የምግብ ፊላጎቱ በያዝነዉ የፈረንጆቹ ዓመት ሐምሌና ነሃሴ ወር ላይ እንደካለፈዉ ግንቦት ወር ጀምሮ በመጠንም በስርጭትም ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በመጣሉ በምሥራቅ አፍሪቃ ሃገራት ከባድ ችግር ማስከተሉ ይታወሳል።

Dürre in Ostafrika: Äthiopien
ምስል AP

ይህንን ለመከላከል በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ሰፊ ጥረት ተደርገዋል የሚሉት በእርሻ ሚኒስቴር የህዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ አልማየሁ ብርኃኑ ናቸዉ። አቶ አለማየሁ «መንግስት ይህን ችግር ለመቋቋም ከ10 ብሊዮን ብር በላይ» የምግብ እጥረቱን ለመፍታት እየተሯሯጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በ50 ዓመት ዉስጥ በጣም ካባድ የሚባለዉ ይህ ድርቅ በመከሰቱ በሰዉ ሕይወትና በእንስሳ ላይ ከባድ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ዘገባዎች ያሳያሉ። በኢትዮጵያ ድርቁ ባስከተለዉ የምግብ እጥረት ከአምስቱ የቅድመ ማስጠንቀቅያ ምድቦች «አስቸኳይ» ተብሎ የሚጠራዉ የኦሮሚያ፤ አፋር ፤ ሶማሊያና አማራ ክልሎች በአራተኛ ምድብ ዉስጥ እንደሚገኙ የረሃብ ቅድመ-ማስጠንቀቅያ ኔትዎርክ ዘገባ ያሳያል። በጊዜ መፍቴ ካላገኘ በስተቀር እነዚህ ክልሎች ወደ አምስተኛዉ ምድብ፣ ማለትም ወደ «ራሃብ»፣ ሊሻጋጋሩ እንደሚችሉም ያስጠነቅቃል።


የምግብ እጥረት ብከሰትም ባይከሰትም የመጠባበቅያ እህል ክምችት እንዳለ ከተናገሩ በኋላ የዝናብ ሁኔታዉ ከተሻሻለ ለአገር ዉስጭ ፍጆታ እንደሚዉል ግን ችግሩ የሚባባስ ከሆነ ሰዎችን የመታደግ እንደሚዉል አቶ አለማየሁ ተናግረዋል። በዶቼ-ቬሌ የፊስ ቡክ ደረ-ገፅ ይሄን ጉዳይ አስመልክቶ በተደረገዉ ዉይይት አብዛኞች ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂ መንግስትን አድርገዋል። የደረሱን አስተያየቶች፤ ኢትዮጵያ አደገች፣ ሁለት ዲጅት ኤኮነሚ ላይ የምትገኝ አገር ናት እየተባለ 15 ሚሊዮን ህዝብ ለምግብ እጥረት መዳረጉ እንዳሳዘናቸዉ ነዉ፤ የሚያሳዩት። ይህ ችግር ቀደም ብሎ ስለተሰከሰተ ይላሉ አስታያየት ሰጨዎቹ መንግስት ሰብዓዊ ርዳታ ለመስጠት ዘግይቷል፣ ለሚዲያ በሩን በመዝጋቱ ምክንያት የድርቁ መጠን ግልፅ አልተደረገም እናም ሰብዓዊ ርዳታ ሰጪ ድርጅቶችን በአዋጅ መከልከሉ ችግሩን አባብሶታል ሲሉ ፅፈዋል።

Dürre in Ostafrika: Äthiopien
ምስል AP


መርጋ ዮናስ
አዜብ ታደሰ